الشعراء
Ash-Shu'araa
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
طسٓمٓ
Open ayah 26:1ጠ.ሰ.መ. (ጧ ሲን ሚም)፡፡
تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُبِينِ
Open ayah 26:2ይህች ግልጽ ከኾነው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡
لَعَلَّكَ بَٰخِعٞ نَّفۡسَكَ أَلَّا يَكُونُواْ مُؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:3አማኞች ባለመኾናቸው፤ (በቁጭት) ነፍስህን ገዳይ መኾን ይፈራልሃል፡፡
إِن نَّشَأۡ نُنَزِّلۡ عَلَيۡهِم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ ءَايَةٗ فَظَلَّتۡ أَعۡنَٰقُهُمۡ لَهَا خَٰضِعِينَ
Open ayah 26:4ብንሻ በእነሱ ላይ ከሰማይ ተዓምረን እናወርድና አንገቶቻቸው (መሪዎቻቸው) ለእርሷ ተዋራጆች ይኾናሉ፡፡
وَمَا يَأۡتِيهِم مِّن ذِكۡرٖ مِّنَ ٱلرَّحۡمَٰنِ مُحۡدَثٍ إِلَّا كَانُواْ عَنۡهُ مُعۡرِضِينَ
Open ayah 26:5ከአልረሕማንም ዘንድ ኣዲስ የተወረደ ቁርኣን አይመጣላቸውም፤ ከእርሱ የሚሸሹ ቢኾኑ እንጂ፡፡
فَقَدۡ كَذَّبُواْ فَسَيَأۡتِيهِمۡ أَنۢبَٰٓؤُاْ مَا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
Open ayah 26:6በእርግጥም አስተባበሉ፡፡ የዚያም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ወሬዎች (ፍጻሜ) ይመጣባቸዋል፡፡
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَى ٱلۡأَرۡضِ كَمۡ أَنۢبَتۡنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوۡجٖ كَرِيمٍ
Open ayah 26:7ወደ ምድርም በውስጧ ከመልካም (በቃይ) ጎሳ ሁሉ ብዙን እንዳበቀልን አላዩምን፡፡
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:8በዚህ አስደናቂ ምልክት አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም አማኞች አልነበሩም፡፡
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
Open ayah 26:9ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊ አዛኝ ነው፡፡
وَإِذۡ نَادَىٰ رَبُّكَ مُوسَىٰٓ أَنِ ٱئۡتِ ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Open ayah 26:10ጌታህም ሙሳን «ወደ በደለኞቹ ሕዝቦች ኺድ» በማለት በጠራው ጊዜ (አስታውስ)፡፡
قَوۡمَ فِرۡعَوۡنَۚ أَلَا يَتَّقُونَ
Open ayah 26:11«ወደ ፈርዖን ሕዝቦች (ኺድ) አላህን አይፈሩምን» (አለው)፡፡
قَالَ رَبِّ إِنِّيٓ أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ
Open ayah 26:12(ሙሳም) አለ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁ፡፡
وَيَضِيقُ صَدۡرِي وَلَا يَنطَلِقُ لِسَانِي فَأَرۡسِلۡ إِلَىٰ هَٰرُونَ
Open ayah 26:13«ልቤም ይጠብባል፡፡ ምላሴም አይፈታም፡፡ ስለዚህ ወደ ሃሩን ላክ፡፡
وَلَهُمۡ عَلَيَّ ذَنۢبٞ فَأَخَافُ أَن يَقۡتُلُونِ
Open ayah 26:14«ለእነርሱም በእኔ ላይ (የደም) ወንጀል አልለ፡፡ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ፡፡»
قَالَ كَلَّاۖ فَٱذۡهَبَا بِـَٔايَٰتِنَآۖ إِنَّا مَعَكُم مُّسۡتَمِعُونَ
Open ayah 26:15(አላህ) አለ «ተው! (አይነኩህም)፡፡ በተዓምራቶቻችንም ኺዱ፡፡ እኛ ከእናንተ ጋር ሰሚዎች ነንና፡፡
فَأۡتِيَا فِرۡعَوۡنَ فَقُولَآ إِنَّا رَسُولُ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:16«ወደ ፈርዖንም ኺዱ፡፡ በሉትም፡- እኛ የዓለማት ጌታ መልክተኞች ነን፡፡
أَنۡ أَرۡسِلۡ مَعَنَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
Open ayah 26:17«የእስራኤልን ልጆች ከእኛ ጋር ልቀቅ፡፡»
قَالَ أَلَمۡ نُرَبِّكَ فِينَا وَلِيدٗا وَلَبِثۡتَ فِينَا مِنۡ عُمُرِكَ سِنِينَ
Open ayah 26:18(ፈርዖንም) አለ «ልጅ ኾነህ በእኛ ውስጥ አላሳደግንህምን በእኛ ውስጥም ከዕድሜህ ብዙ ዓመታትን አልተቀመጥክምን
وَفَعَلۡتَ فَعۡلَتَكَ ٱلَّتِي فَعَلۡتَ وَأَنتَ مِنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
Open ayah 26:19«ያችንም የሠራሃትን ሥራህን አልሠራህምን አንተም ከውለታ ቢሶቹ ነህ» (አለ)፡፡
قَالَ فَعَلۡتُهَآ إِذٗا وَأَنَا۠ مِنَ ٱلضَّآلِّينَ
Open ayah 26:20(ሙሳም) አለ «ያን ጊዜ እኔም ከተሳሳቱት ኾኜ ሠራኋት፡፡
فَفَرَرۡتُ مِنكُمۡ لَمَّا خِفۡتُكُمۡ فَوَهَبَ لِي رَبِّي حُكۡمٗا وَجَعَلَنِي مِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 26:21«በፈራኋችሁም ጊዜ ከእንናተ ሸሸሁ፡፡ ጌታየም ለእኔ ጥበብን ሰጠኝ፡፡ ከመልክተኞቹም አደረገኝ፡፡
وَتِلۡكَ نِعۡمَةٞ تَمُنُّهَا عَلَيَّ أَنۡ عَبَّدتَّ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
Open ayah 26:22«ይህችም የእስራኤልን ልጆች ባሪያ በማድረግህ በእኔ ላይ የምትመጻደቅባት ጸጋ ነት፡፡»
قَالَ فِرۡعَوۡنُ وَمَا رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:23ፈርዖን አለ «(ላከኝ የምትለው) የዓለማትም ጌታ ምንድነው»
قَالَ رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَآۖ إِن كُنتُم مُّوقِنِينَ
Open ayah 26:24(ሙሳ) «የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምታረጋግጡ ብትኾኑ (ነገሩ ይህ ነው)፤» አለው፡፡
قَالَ لِمَنۡ حَوۡلَهُۥٓ أَلَا تَسۡتَمِعُونَ
Open ayah 26:25(ፈርዖንም) በዙሪያው ላሉት ሰዎች «አትሰሙምን» አለ፡፡
قَالَ رَبُّكُمۡ وَرَبُّ ءَابَآئِكُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ
Open ayah 26:26(ሙሳ) «ጌታችሁና የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው» አለው፡፡
قَالَ إِنَّ رَسُولَكُمُ ٱلَّذِيٓ أُرۡسِلَ إِلَيۡكُمۡ لَمَجۡنُونٞ
Open ayah 26:27(ፈርዖን) «ያ ወደእናንተ የተላከው መልክተኛችሁ በእርግጥ ዕብድ ነው» አለ፡፡
قَالَ رَبُّ ٱلۡمَشۡرِقِ وَٱلۡمَغۡرِبِ وَمَا بَيۡنَهُمَآۖ إِن كُنتُمۡ تَعۡقِلُونَ
Open ayah 26:28(ሙሳ) «የምሥራቅና የምዕራብ በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ ታውቁ እንደኾናችሁ (እመኑበት)» አለው፡፡
قَالَ لَئِنِ ٱتَّخَذۡتَ إِلَٰهًا غَيۡرِي لَأَجۡعَلَنَّكَ مِنَ ٱلۡمَسۡجُونِينَ
Open ayah 26:29(ፈርዖን) «ከእኔ ሌላ አምላክን ብትይዝ በውነቱ ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ» አለ፡፡
قَالَ أَوَلَوۡ جِئۡتُكَ بِشَيۡءٖ مُّبِينٖ
Open ayah 26:30(ሙሳ) «በግልጽ አስረጅ ብመጣህም እንኳ» አለው፡፡
قَالَ فَأۡتِ بِهِۦٓ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
Open ayah 26:31«እንግዲያውስ ከእውነተኞች እንደኾንክ (አስረጁን) አምጣው» አለ፡፡
فَأَلۡقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعۡبَانٞ مُّبِينٞ
Open ayah 26:32በትሩንም ጣለ፡፡ እርሷም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ኾነች፡፡
وَنَزَعَ يَدَهُۥ فَإِذَا هِيَ بَيۡضَآءُ لِلنَّٰظِرِينَ
Open ayah 26:33እጁንም አወጣ፡፡ ወዲያውም እርሷ ለተመልካቾች (የምታበራ) ነጭ ኾነች፡፡
قَالَ لِلۡمَلَإِ حَوۡلَهُۥٓ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌ عَلِيمٞ
Open ayah 26:34(ፈርዖን) በዙሪያው ላሉት መማክርት «ይህ በእርግጥ ዐዋቂ ድግምተኛ ነው» አለ፡፡
يُرِيدُ أَن يُخۡرِجَكُم مِّنۡ أَرۡضِكُم بِسِحۡرِهِۦ فَمَاذَا تَأۡمُرُونَ
Open ayah 26:35«ከምድራችሁ በድግምቱ ሊያወጣችሁ ይፈልጋልና ምንን ታዛላችሁ» (አላቸው)፡፡
قَالُوٓاْ أَرۡجِهۡ وَأَخَاهُ وَٱبۡعَثۡ فِي ٱلۡمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ
Open ayah 26:36አሉት «እርሱን ወንድሙንም አቆይና በየከተሞቹ ሰብሳቢዎችን ላክ፡፡
يَأۡتُوكَ بِكُلِّ سَحَّارٍ عَلِيمٖ
Open ayah 26:37«በጣም ዐዋቂ ድግምተኞችን ሁሉ ያመጡልሃልና፡፡»
فَجُمِعَ ٱلسَّحَرَةُ لِمِيقَٰتِ يَوۡمٖ مَّعۡلُومٖ
Open ayah 26:38ድግምተኞቹም በታወቀ ቀን ቀጠሮ ተሰበሰቡ፡፡
وَقِيلَ لِلنَّاسِ هَلۡ أَنتُم مُّجۡتَمِعُونَ
Open ayah 26:39ለሰዎቹም «እናንተ ተሰብስባችኋልን» ተባለ፡፡
لَعَلَّنَا نَتَّبِعُ ٱلسَّحَرَةَ إِن كَانُواْ هُمُ ٱلۡغَٰلِبِينَ
Open ayah 26:40«ድግምተኞቹን እነሱ አሸናፊዎች ቢኾኑ እንከተል ዘንድ» (ተባለ)፡፡
فَلَمَّا جَآءَ ٱلسَّحَرَةُ قَالُواْ لِفِرۡعَوۡنَ أَئِنَّ لَنَا لَأَجۡرًا إِن كُنَّا نَحۡنُ ٱلۡغَٰلِبِينَ
Open ayah 26:41«ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ለፈርዖን እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለእኛ በእርግጥ ዋጋ አለን» አሉት፡፡
قَالَ نَعَمۡ وَإِنَّكُمۡ إِذٗا لَّمِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ
Open ayah 26:42«አዎን፤ እናንተም ያን ጊዜ ከባለሟሎቹ ትኾናላችሁ» አላቸው፡፡
قَالَ لَهُم مُّوسَىٰٓ أَلۡقُواْ مَآ أَنتُم مُّلۡقُونَ
Open ayah 26:43ሙሳ «ለእነርሱ እናንተ የምትጥሉትን ጣሉ» አላቸው፡፡
فَأَلۡقَوۡاْ حِبَالَهُمۡ وَعِصِيَّهُمۡ وَقَالُواْ بِعِزَّةِ فِرۡعَوۡنَ إِنَّا لَنَحۡنُ ٱلۡغَٰلِبُونَ
Open ayah 26:44ገመዶቻቸውንና በትሮቻቸውንም ጣሉ፡፡ «በፈርዖንም ክብር ይኹንብን፡፡ እኛ በእርግጥ አሸናፊዎቹ እኛ ነን» አሉ፡፡
فَأَلۡقَىٰ مُوسَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ تَلۡقَفُ مَا يَأۡفِكُونَ
Open ayah 26:45ሙሳም በትሩን ጣለ፡፡ ወዲያውም እርሷ የሚያስመስሉትን ሁሉ ትውጣለች፡፡
فَأُلۡقِيَ ٱلسَّحَرَةُ سَٰجِدِينَ
Open ayah 26:46ድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ፡፡
قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:47(እነሱም) አሉ «በዓለማት ጌታ አመንን፡፡
رَبِّ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ
Open ayah 26:48«በሙሳና በሃሩን ጌታ፡፡»
قَالَ ءَامَنتُمۡ لَهُۥ قَبۡلَ أَنۡ ءَاذَنَ لَكُمۡۖ إِنَّهُۥ لَكَبِيرُكُمُ ٱلَّذِي عَلَّمَكُمُ ٱلسِّحۡرَ فَلَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَۚ لَأُقَطِّعَنَّ أَيۡدِيَكُمۡ وَأَرۡجُلَكُم مِّنۡ خِلَٰفٖ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمۡ أَجۡمَعِينَ
Open ayah 26:49(ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን እርሱ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ታላቃችሁ ነው፡፡ ወደፊትም (የሚያገኛችሁን) በእርግጥ ታውቃላችሁ፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን (ቀኝና ግራን) በማናጋት እቆረርጣለሁ፡፡ ሁላችሁንም እሰቅላችኋለሁም» አለ፡፡
قَالُواْ لَا ضَيۡرَۖ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ
Open ayah 26:50(እነርሱም) አሉ «ጉዳት የለብንም፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን፡፡
إِنَّا نَطۡمَعُ أَن يَغۡفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَٰيَٰنَآ أَن كُنَّآ أَوَّلَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:51«እኛ የምእምናን መጀመሪያ በመኾናችን ጌታችን ኀጢአቶቻችንን ለእኛ ሊምር እንከጅላለን፡፡»
۞وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنۡ أَسۡرِ بِعِبَادِيٓ إِنَّكُم مُّتَّبَعُونَ
Open ayah 26:52ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ ሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና» ስንል ላክን፡፡
فَأَرۡسَلَ فِرۡعَوۡنُ فِي ٱلۡمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ
Open ayah 26:53ፈርዖንም በየከተሞቹ ሰብሳቢዎችን (እንዲህ ሲል) ላከ፡፡
إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَشِرۡذِمَةٞ قَلِيلُونَ
Open ayah 26:54«እነዚህ ጥቂቶች ጭፈሮች ናቸው፡፡
وَإِنَّهُمۡ لَنَا لَغَآئِظُونَ
Open ayah 26:55«እነርሱም ለእኛ አስቆጪዎች ናቸው፡፡
وَإِنَّا لَجَمِيعٌ حَٰذِرُونَ
Open ayah 26:56«እኛም ብዙዎች ጥንቁቆች ነን፤» (አለ)፡፡
فَأَخۡرَجۡنَٰهُم مِّن جَنَّٰتٖ وَعُيُونٖ
Open ayah 26:57አወጣናቸውም፡፡ ከአትክልቶችና ከምንጮች፡፡
وَكُنُوزٖ وَمَقَامٖ كَرِيمٖ
Open ayah 26:58ከድልቦችም ከመልካም መቀመጫዎችም፡፡
كَذَٰلِكَۖ وَأَوۡرَثۡنَٰهَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
Open ayah 26:59እንደዚሁ ለእስራኤል ልጆች አወረስናትም፡፡
فَأَتۡبَعُوهُم مُّشۡرِقِينَ
Open ayah 26:60ፀሐይዋ ስትወጣም ተከተሉዋቸው፡፡
فَلَمَّا تَرَٰٓءَا ٱلۡجَمۡعَانِ قَالَ أَصۡحَٰبُ مُوسَىٰٓ إِنَّا لَمُدۡرَكُونَ
Open ayah 26:61ሁለቱ ጭፍሮችም በተያዩ ጊዜ የሙሳ ጓዶች «እኛ(የፈርዖን ሰዎች) የሚደርሱብን ነን» አሉ፡፡
قَالَ كَلَّآۖ إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهۡدِينِ
Open ayah 26:62(ሙሳ) «ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» አለ፡፡
فَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنِ ٱضۡرِب بِّعَصَاكَ ٱلۡبَحۡرَۖ فَٱنفَلَقَ فَكَانَ كُلُّ فِرۡقٖ كَٱلطَّوۡدِ ٱلۡعَظِيمِ
Open ayah 26:63ወደ ሙሳም «ባሕሩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክንበት፡፡ (መታውና) ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ፡፡
وَأَزۡلَفۡنَا ثَمَّ ٱلۡأٓخَرِينَ
Open ayah 26:64እዚያም ዘንድ ሌሎችን አቀረብን፡፡
وَأَنجَيۡنَا مُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ
Open ayah 26:65ሙሳንም ከእርሱ ገር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም አዳን፡፡
ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ
Open ayah 26:66ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:67በዚህ ውስጥ ታላቅ ታምር አለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም አማኞች አልነበሩም፡፡
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
Open ayah 26:68ጌታህም እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
وَٱتۡلُ عَلَيۡهِمۡ نَبَأَ إِبۡرَٰهِيمَ
Open ayah 26:69በእነሱም (በሕዝቦችህ) ላይ የኢብራሂምን ወሬ አንብብላቸው፡፡
إِذۡ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦ مَا تَعۡبُدُونَ
Open ayah 26:70ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ትግገዛላችሁ» ባለ ጊዜ፡፡
قَالُواْ نَعۡبُدُ أَصۡنَامٗا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ
Open ayah 26:71«ጣዖታትን እንገዛለን፤ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን» አሉ፡፡
قَالَ هَلۡ يَسۡمَعُونَكُمۡ إِذۡ تَدۡعُونَ
Open ayah 26:72(እርሱም) አለ «በጠራችኋቸው ጊዜ ይሰሟችኋልን
أَوۡ يَنفَعُونَكُمۡ أَوۡ يَضُرُّونَ
Open ayah 26:73«ወይስ ይጠቅሟችኋልን ወይስ ይጎዷችኋልን»
قَالُواْ بَلۡ وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا كَذَٰلِكَ يَفۡعَلُونَ
Open ayah 26:74«የለም! አባቶቻችን እንደዚሁ ሲሠሩ አገኘን» አሉት፡፡
قَالَ أَفَرَءَيۡتُم مَّا كُنتُمۡ تَعۡبُدُونَ
Open ayah 26:75«ትግገዙት የነበራችሁትን አስተዋላችሁን
أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُمُ ٱلۡأَقۡدَمُونَ
Open ayah 26:76«እናንተም የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁም (የተግገዛችሁትን)፡፡»
فَإِنَّهُمۡ عَدُوّٞ لِّيٓ إِلَّا رَبَّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:77«እነሱም (ጣዖቶቹ) ለእኔ ጠላቶች ናቸው፡፡ ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር (እርሱ ወዳጄ ነው)፡፡
ٱلَّذِي خَلَقَنِي فَهُوَ يَهۡدِينِ
Open ayah 26:78«(እርሱ) ያ የፈጠረኝ ነው፡፡ እርሱም ይመራኛል፡፡
وَٱلَّذِي هُوَ يُطۡعِمُنِي وَيَسۡقِينِ
Open ayah 26:79«ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝ ነው፡፡
وَإِذَا مَرِضۡتُ فَهُوَ يَشۡفِينِ
Open ayah 26:80«በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል፡፡
وَٱلَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحۡيِينِ
Open ayah 26:81«ያም የሚገድለኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው፡፡
وَٱلَّذِيٓ أَطۡمَعُ أَن يَغۡفِرَ لِي خَطِيٓـَٔتِي يَوۡمَ ٱلدِّينِ
Open ayah 26:82ያም በፍርዱ ቀን ኀጢአቴን ለእኔ ሊምር የምከጅለው ነው፡፡
رَبِّ هَبۡ لِي حُكۡمٗا وَأَلۡحِقۡنِي بِٱلصَّٰلِحِينَ
Open ayah 26:83ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ስጠኝ! በደጋጎቹም ሰዎች አስጠጋኝ፡፡
وَٱجۡعَل لِّي لِسَانَ صِدۡقٖ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ
Open ayah 26:84በኋለኞቹም ሕዝቦች ውስጥ ለእኔ መልካም ዝናን አድርግልኝ፡፡
وَٱجۡعَلۡنِي مِن وَرَثَةِ جَنَّةِ ٱلنَّعِيمِ
Open ayah 26:85የጸጋይቱን ገነት ከሚወርሱትም አድርገኝ፡፡
وَٱغۡفِرۡ لِأَبِيٓ إِنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلضَّآلِّينَ
Open ayah 26:86ለአባቴም ማር፡፡ እርሱ ከተሳሳቱት ነበረና፡፡
وَلَا تُخۡزِنِي يَوۡمَ يُبۡعَثُونَ
Open ayah 26:87በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ፡፡
يَوۡمَ لَا يَنفَعُ مَالٞ وَلَا بَنُونَ
Open ayah 26:88ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡
إِلَّا مَنۡ أَتَى ٱللَّهَ بِقَلۡبٖ سَلِيمٖ
Open ayah 26:89ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡»
وَأُزۡلِفَتِ ٱلۡجَنَّةُ لِلۡمُتَّقِينَ
Open ayah 26:90ገነትም ለፈሪዎች በምትቀረብበት (ቀን)፡፡
وَبُرِّزَتِ ٱلۡجَحِيمُ لِلۡغَاوِينَ
Open ayah 26:91ገሀነምም ለጠመሞች በምትገለጽበት (ቀን)፡፡
وَقِيلَ لَهُمۡ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡ تَعۡبُدُونَ
Open ayah 26:92ለእነሱም በሚባል ቀን «ትግገዟቸው የነበራችሁት የት ናቸው»
مِن دُونِ ٱللَّهِ هَلۡ يَنصُرُونَكُمۡ أَوۡ يَنتَصِرُونَ
Open ayah 26:93«ከአላህ ሌላ ሲኾኑ ይረዱዋችኋልን ወይስ (ለራሳቸው) ይርረዳሉን»
فَكُبۡكِبُواْ فِيهَا هُمۡ وَٱلۡغَاوُۥنَ
Open ayah 26:94በውስጧም እነሱና ጠማሞቹ በፊቶቻቸው ተጥለው ይንከባለላሉ፡፡
وَجُنُودُ إِبۡلِيسَ أَجۡمَعُونَ
Open ayah 26:95የሰይጣንም ሰራዊቶች መላውም (ይጣላሉ)፡፡
قَالُواْ وَهُمۡ فِيهَا يَخۡتَصِمُونَ
Open ayah 26:96እነርሱም በእርሷ ውስጥ የሚከራከሩ ኾነው ይላሉ፡-
تَٱللَّهِ إِن كُنَّا لَفِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ
Open ayah 26:97በአላህ እንምላለን፤ እኛ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነበርን፡፡
إِذۡ نُسَوِّيكُم بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:98(ጣዖቶቹን) በዓለማት ጌታ ባስተካከልናችሁ ጊዜ፡፡
وَمَآ أَضَلَّنَآ إِلَّا ٱلۡمُجۡرِمُونَ
Open ayah 26:99አመጸኞቹም እንጅ ሌላ አላሳሳተንም፡፡
فَمَا لَنَا مِن شَٰفِعِينَ
Open ayah 26:100ከአማላጆችም ለእኛ ምንም የለንም፡፡
وَلَا صَدِيقٍ حَمِيمٖ
Open ayah 26:101አዛኝ ወዳጂም (የለንም)፡፡
فَلَوۡ أَنَّ لَنَا كَرَّةٗ فَنَكُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:102ለእኛም አንዲት ጊዜ መመለስ በኖረችንና ከአማኞቹ በኾን እንመኛለን (ይላሉ)፡፡
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:103በዚህ ውስጥ አስደናቂ ግሳጼ አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም አማኞች አልነበሩም፡፡
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
Open ayah 26:104ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
كَذَّبَتۡ قَوۡمُ نُوحٍ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 26:105የኑሕ ሕዝቦች መልክተኞችን አስተባበሉ፡፡
إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ نُوحٌ أَلَا تَتَّقُونَ
Open ayah 26:106ወንድማቸው ኑሕ ለእነሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን
إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
Open ayah 26:107«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
Open ayah 26:108«አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም፡፡
وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:109«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
Open ayah 26:110«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡»
۞قَالُوٓاْ أَنُؤۡمِنُ لَكَ وَٱتَّبَعَكَ ٱلۡأَرۡذَلُونَ
Open ayah 26:111(እነርሱም) «ወራዶቹ የተከተሉህ ኾነህ ለአንተ እናምናለን» አሉት፡፡
قَالَ وَمَا عِلۡمِي بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
Open ayah 26:112(እርሱም) አላቸው «ይሠሩት በነበሩት ነገር ምን ዕውቀት አለኝ፡፡
إِنۡ حِسَابُهُمۡ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّيۖ لَوۡ تَشۡعُرُونَ
Open ayah 26:113«ምርመራቸው በጌታዬ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ ብታውቁ ኖሮ (ይህንን ትርረዱ ነበር)፡፡
وَمَآ أَنَا۠ بِطَارِدِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:114«እኔም አማኞችን አባራሪ አይደለሁም፡፡
إِنۡ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٞ مُّبِينٞ
Open ayah 26:115«እኔ ግልጽ አስፈራሪ እንጅ ሌላ አይደለሁም፡፡»
قَالُواْ لَئِن لَّمۡ تَنتَهِ يَٰنُوحُ لَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمَرۡجُومِينَ
Open ayah 26:116«ኑሕ ሆይ! (ከምትለው) ባትከለከል በእርግጥ ከሚወገሩት ትኾናለህ» አሉት፡፡
قَالَ رَبِّ إِنَّ قَوۡمِي كَذَّبُونِ
Open ayah 26:117(እርሱም) አለ «ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ አስተባበሉኝ፡፡
فَٱفۡتَحۡ بَيۡنِي وَبَيۡنَهُمۡ فَتۡحٗا وَنَجِّنِي وَمَن مَّعِيَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:118«በእኔና በእነርሱም መካከል (ተገቢ) ፍርድን ፍረድ፡፡ አድነኝም፡፡ ከእኔ ጋር ያሉትንም ምእምናን፡፡»
فَأَنجَيۡنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ فِي ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ
Open ayah 26:119እርሱንም ከእርሱ ጋር ያለውንም ሁሉ በተመላው መርከብ ውስጥ አዳን፡፡
ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا بَعۡدُ ٱلۡبَاقِينَ
Open ayah 26:120ከዚያም በኋላ ቀሪዎቹን አሰጠምን፡፡
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:121በዚህ ውስጥ ታላቅ ግሳጼ አለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም አማኞች አልነበሩም፡፡
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
Open ayah 26:122ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
كَذَّبَتۡ عَادٌ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 26:123ዓድ መልክተኞችን አስተባበለች፡፡
إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ هُودٌ أَلَا تَتَّقُونَ
Open ayah 26:124ወንድማቸው ሁድ ለነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን
إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
Open ayah 26:125«እኔ ለናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
Open ayah 26:126«አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም፡፡
وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:127«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
أَتَبۡنُونَ بِكُلِّ رِيعٍ ءَايَةٗ تَعۡبَثُونَ
Open ayah 26:128«የምትጫወቱ ኾናችሁ በከፍተኛ ስፍራ ሁሉ ላይ ምልክትን ትገነባላችሁን
وَتَتَّخِذُونَ مَصَانِعَ لَعَلَّكُمۡ تَخۡلُدُونَ
Open ayah 26:129«የውሃ ማጠራቀሚያዎችንና ሕንፃዎችንም ዘላለም መኖርን የምትከጅሉ ኾናችሁ ትሠራላችሁን
وَإِذَا بَطَشۡتُم بَطَشۡتُمۡ جَبَّارِينَ
Open ayah 26:130«በቀጣችሁም ጊዜ ጨካኞች ኾናችሁ ትቀጣላችሁን
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
Open ayah 26:131«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
وَٱتَّقُواْ ٱلَّذِيٓ أَمَدَّكُم بِمَا تَعۡلَمُونَ
Open ayah 26:132«ያንንም በምታውቁት (ጸጋ) ያጣቀማችሁን ፍሩ፡፡
أَمَدَّكُم بِأَنۡعَٰمٖ وَبَنِينَ
Open ayah 26:133«በእንስሳዎችና በልጆች ያጣቀማችሁን፡፡
وَجَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ
Open ayah 26:134«በአትክልቶችና በምንጮችም፡፡
إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
Open ayah 26:135«እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁና፡፡»
قَالُواْ سَوَآءٌ عَلَيۡنَآ أَوَعَظۡتَ أَمۡ لَمۡ تَكُن مِّنَ ٱلۡوَٰعِظِينَ
Open ayah 26:136(እነርሱም) አሉ «ብትገስጽም ወይም ከገሳጮቹ ባትኾንም በእኛ ላይ እኩል ነው፤ (ያለንበትን አንለቅም)፡፡
إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا خُلُقُ ٱلۡأَوَّلِينَ
Open ayah 26:137«ይህ የፊተኞቹ ሰዎች ፀባይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
وَمَا نَحۡنُ بِمُعَذَّبِينَ
Open ayah 26:138«እኛም የምንቅቀጣ አይደለንም» (አሉ)፡፡
فَكَذَّبُوهُ فَأَهۡلَكۡنَٰهُمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:139አስተባበሉትም፡፡ አጠፋናቸውም፡፡ በዚህም ውስጥ እርግጠኛ ግሳጼ አለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእመናን አልነበሩም፡፡
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
Open ayah 26:140ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
كَذَّبَتۡ ثَمُودُ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 26:141ሰሙድ መልክተኞችን አስተባበለች፡፡
إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ صَٰلِحٌ أَلَا تَتَّقُونَ
Open ayah 26:142ወንድማቸው ሷሊህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን
إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
Open ayah 26:143«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
Open ayah 26:144«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:145«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
أَتُتۡرَكُونَ فِي مَا هَٰهُنَآ ءَامِنِينَ
Open ayah 26:146«በዚያ እዚህ ባለው (ጸጋ) ውስጥ የረካችሁ ኾናችሁ ትተዋላችሁን
فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٖ
Open ayah 26:147«በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ፡፡
وَزُرُوعٖ وَنَخۡلٖ طَلۡعُهَا هَضِيمٞ
Open ayah 26:148«በአዝመራዎችም ፍሬዋ የበሰለ በኾነች ዘንባባም፤ (ውስጥ ትተዋላችሁን)
وَتَنۡحِتُونَ مِنَ ٱلۡجِبَالِ بُيُوتٗا فَٰرِهِينَ
Open ayah 26:149«ብልሆች ኾናችሁ ከጋራዎች ቤቶችንም ትጠርባላችሁ፡፡
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
Open ayah 26:150«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
وَلَا تُطِيعُوٓاْ أَمۡرَ ٱلۡمُسۡرِفِينَ
Open ayah 26:151«የወሰን አላፊዎችንም ትዕዛዝ አትከተሉ፡፡
ٱلَّذِينَ يُفۡسِدُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا يُصۡلِحُونَ
Open ayah 26:152«የእነዚያን በምድር ላይ የሚያጠፉትንና የማያበጁትን፡፡»
قَالُوٓاْ إِنَّمَآ أَنتَ مِنَ ٱلۡمُسَحَّرِينَ
Open ayah 26:153(እነሱም) አሉ «አንተ በብዙ ከተደገመባቸው ሰዎች ብቻ ነህ፡፡
مَآ أَنتَ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا فَأۡتِ بِـَٔايَةٍ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
Open ayah 26:154«አንተ ብጤያችን ሰው እንጅ ሌላ አይደለህም፡፡ ከእውነተኞቹም እንደኾንክ ተዓምርን አምጣ፡፡»
قَالَ هَٰذِهِۦ نَاقَةٞ لَّهَا شِرۡبٞ وَلَكُمۡ شِرۡبُ يَوۡمٖ مَّعۡلُومٖ
Open ayah 26:155(እርሱም) አለ «ይህች ግመል ናት፡፡ ለእርሷ የመጠጥ ፋንታ አላት፡፡ ለእናንተም የታወቀ ቀን ፋንታ አላችሁ፡፡
وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٖ فَيَأۡخُذَكُمۡ عَذَابُ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
Open ayah 26:156«በክፉም አትንኳት፡፡ የታላቅ ቀን ቅጣት ይይዛችኋልና፡፡»
فَعَقَرُوهَا فَأَصۡبَحُواْ نَٰدِمِينَ
Open ayah 26:157ወጓትም፡፡ ወዲያውም ተጸጻቾች ኾነው አነጉ፡፡
فَأَخَذَهُمُ ٱلۡعَذَابُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:158ቅጣቱም ያዛቸው፡፡ በዚህም ውስጥ ግሳፄ አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእመናን አልነበሩም፡፡
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
Open ayah 26:159ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
كَذَّبَتۡ قَوۡمُ لُوطٍ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 26:160የሉጥ ሕዝቦች መልክተኞችን አስተባባሉ፡፡
إِذۡ قَالَ لَهُمۡ أَخُوهُمۡ لُوطٌ أَلَا تَتَّقُونَ
Open ayah 26:161ወንድማቸው ሉጥ ለእነርሱ ባለ ጊዜ «አትጠነቀቁምን
إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
Open ayah 26:162«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
Open ayah 26:163«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:164«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
أَتَأۡتُونَ ٱلذُّكۡرَانَ مِنَ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:165«ከዓለማት ሰዎች ወንዶችን ትመጣላችሁን
وَتَذَرُونَ مَا خَلَقَ لَكُمۡ رَبُّكُم مِّنۡ أَزۡوَٰجِكُمۚ بَلۡ أَنتُمۡ قَوۡمٌ عَادُونَ
Open ayah 26:166«ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦ ናችሁ፡፡»
قَالُواْ لَئِن لَّمۡ تَنتَهِ يَٰلُوطُ لَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُخۡرَجِينَ
Open ayah 26:167(እነርሱም) አሉ «ሉጥ ሆይ! ባትከለከል በእርግጥ (ከአገር) ከሚወጡት ትኾናለህ፡፡»
قَالَ إِنِّي لِعَمَلِكُم مِّنَ ٱلۡقَالِينَ
Open ayah 26:168(እርሱም) አለ «እኔ ሥራችሁን ከሚጠሉት ሰዎች ነኝ፡፡
رَبِّ نَجِّنِي وَأَهۡلِي مِمَّا يَعۡمَلُونَ
Open ayah 26:169«ጌታዬ ሆይ! እኔንም ቤተሰቦቼንም ከሚሠሩት ሥራ (ቅጣት) አድነን፡፡»
فَنَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ
Open ayah 26:170እርሱንም ቤተሰቦቹንም በጠቅላላ አዳንናቸው፡፡
إِلَّا عَجُوزٗا فِي ٱلۡغَٰبِرِينَ
Open ayah 26:171በቀሪዎቹ ውስጥ የኾነች አሮጊት ብቻ ስትቀር (እርሷ ጠፋች)፡፡
ثُمَّ دَمَّرۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ
Open ayah 26:172ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡
وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهِم مَّطَرٗاۖ فَسَآءَ مَطَرُ ٱلۡمُنذَرِينَ
Open ayah 26:173በእነሱም ላይ (የድንጋይን) ዝናምን አዘነምንባቸው፡፡ የተስፈራሪዎቹም ዝናም (ምንኛ) ከፋ፡፡
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:174በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዓምር አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእመናን አልነበሩም፡፡
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
Open ayah 26:175ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
كَذَّبَ أَصۡحَٰبُ لۡـَٔيۡكَةِ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 26:176የአይከት ሰዎች መልክተኞችን አስተባበሉ፤
إِذۡ قَالَ لَهُمۡ شُعَيۡبٌ أَلَا تَتَّقُونَ
Open ayah 26:177ሹዕይብ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን
إِنِّي لَكُمۡ رَسُولٌ أَمِينٞ
Open ayah 26:178«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
Open ayah 26:179«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
وَمَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مِنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:180«በርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
۞أَوۡفُواْ ٱلۡكَيۡلَ وَلَا تَكُونُواْ مِنَ ٱلۡمُخۡسِرِينَ
Open ayah 26:181«ስፍርን ሙሉ፡፡ ከአጉዳዮቹም አትኹኑ፡፡
وَزِنُواْ بِٱلۡقِسۡطَاسِ ٱلۡمُسۡتَقِيمِ
Open ayah 26:182«በትክክለኛ ሚዛንም መዝኑ፡፡
وَلَا تَبۡخَسُواْ ٱلنَّاسَ أَشۡيَآءَهُمۡ وَلَا تَعۡثَوۡاْ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُفۡسِدِينَ
Open ayah 26:183«ሰዎችንም ነገሮቻቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ላይ አጥፊዎች ኾናችሁ አታበላሹ፡፡
وَٱتَّقُواْ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ وَٱلۡجِبِلَّةَ ٱلۡأَوَّلِينَ
Open ayah 26:184«ያንንም የፈጠራችሁን የቀድሞዎቹንም ፍጡሮች (የፈጠረውን) ፍሩ፡፡»
قَالُوٓاْ إِنَّمَآ أَنتَ مِنَ ٱلۡمُسَحَّرِينَ
Open ayah 26:185አሉ «አንተ በብዛት ከተደገመባቸው ሰዎች ነህ፡፡
وَمَآ أَنتَ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا وَإِن نَّظُنُّكَ لَمِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ
Open ayah 26:186«አንተም ብጤያችን ሰው እንጅ ሌላ አይደለህም፡፡ እነሆ ከውሸታሞች ነህ ብለን እንጠረጥርሃለን፡፡
فَأَسۡقِطۡ عَلَيۡنَا كِسَفٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
Open ayah 26:187«ከእውነተኞቹም እንደኾንክ በእኛ ላይ ከሰማይ ቁራጭን ጣልብን፡፡»
قَالَ رَبِّيٓ أَعۡلَمُ بِمَا تَعۡمَلُونَ
Open ayah 26:188«ጌታዬ የምትሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፤» አላቸው፡፡
فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَهُمۡ عَذَابُ يَوۡمِ ٱلظُّلَّةِۚ إِنَّهُۥ كَانَ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٍ
Open ayah 26:189አስተባበሉትም፡፡ የጥላይቷ ቀን ቅጣትም ያዛቸው፡፡ እርሱ የከባድ ቀን ቅጣት ነበርና፡፡
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:190በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዓምር አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእምናን አልነበሩም፡፡
وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ
Open ayah 26:191ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
وَإِنَّهُۥ لَتَنزِيلُ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 26:192እርሱም (ቁርኣን) በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡
نَزَلَ بِهِ ٱلرُّوحُ ٱلۡأَمِينُ
Open ayah 26:193እርሱን ታማኙ መንፈስ (ጂብሪል) አወረደው፤
عَلَىٰ قَلۡبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُنذِرِينَ
Open ayah 26:194ከአስፈራሪዎቹ (ነቢያት) ትኾን ዘንድ በልብህ ላይ (አወረደው)፡፡
بِلِسَانٍ عَرَبِيّٖ مُّبِينٖ
Open ayah 26:195ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ፡፡
وَإِنَّهُۥ لَفِي زُبُرِ ٱلۡأَوَّلِينَ
Open ayah 26:196እርሱም (ቁርኣን) በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ (የተወሳ ነው)፡፡
أَوَلَمۡ يَكُن لَّهُمۡ ءَايَةً أَن يَعۡلَمَهُۥ عُلَمَٰٓؤُاْ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ
Open ayah 26:197የእስራኤል ልጆች ሊቃውንት የሚያውቁት መኾኑ ለእነርሱ (ለመካ ከሓዲዎች) ምልክት አይኾናቸውምን
وَلَوۡ نَزَّلۡنَٰهُ عَلَىٰ بَعۡضِ ٱلۡأَعۡجَمِينَ
Open ayah 26:198ከአዕጀሞች ባንዱ ላይ ባወረድነውም ኖሮ፤
فَقَرَأَهُۥ عَلَيۡهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ مُؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:199በእነርሱ ላይ ባነበበውም በእርሱ አማኞች አይኾኑም ነበር፡፡
كَذَٰلِكَ سَلَكۡنَٰهُ فِي قُلُوبِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
Open ayah 26:200እንደዚሁ (ማስተባበልን) በተንኮለኞች ልቦች ውስጥ አስገባነው፡፡
لَا يُؤۡمِنُونَ بِهِۦ حَتَّىٰ يَرَوُاْ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَلِيمَ
Open ayah 26:201አሳማሚ ቅጣትን እስከሚያዩ ድረስ በእርሱ አያምኑም፡፡
فَيَأۡتِيَهُم بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ
Open ayah 26:202እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ (ቅጣቱ) ድንገት እስከሚመጣባቸውም ድረስ (አያምኑም)፡፡
فَيَقُولُواْ هَلۡ نَحۡنُ مُنظَرُونَ
Open ayah 26:203(በመጣባቸው ጊዜ) «እኛ የምንቆይ ነን» እስከሚሉም (አያምኑም)፡፡
أَفَبِعَذَابِنَا يَسۡتَعۡجِلُونَ
Open ayah 26:204በቅጣታችን ያቻኩላሉን
أَفَرَءَيۡتَ إِن مَّتَّعۡنَٰهُمۡ سِنِينَ
Open ayah 26:205አየህን ብዙ ዓመታትን ብናጣቅማቸው፤
ثُمَّ جَآءَهُم مَّا كَانُواْ يُوعَدُونَ
Open ayah 26:206ከዚያም ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቢመጣባቸው፤
مَآ أَغۡنَىٰ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يُمَتَّعُونَ
Open ayah 26:207ይጣቀሙበት የነበሩት ሁሉ ከእነሱ ምንም አያብቃቃቸውም፡፡
وَمَآ أَهۡلَكۡنَا مِن قَرۡيَةٍ إِلَّا لَهَا مُنذِرُونَ
Open ayah 26:208አንዲትንም ከተማ ለእርሷ አስፈራሪዎች ያሏት (እና ያስተባበለች) ኾና እንጅ አላጠፋንም፡፡
ذِكۡرَىٰ وَمَا كُنَّا ظَٰلِمِينَ
Open ayah 26:209(ይህች) ግሳፄ ናት፡፡ በዳዮችም አልነበርንም፡፡
وَمَا تَنَزَّلَتۡ بِهِ ٱلشَّيَٰطِينُ
Open ayah 26:210ሰይጣናትም እርሱን (ቁርኣንን) አላወረዱትም፡፡
وَمَا يَنۢبَغِي لَهُمۡ وَمَا يَسۡتَطِيعُونَ
Open ayah 26:211ለእነርሱም አይገባቸውም፤ አይችሉምም፡፡
إِنَّهُمۡ عَنِ ٱلسَّمۡعِ لَمَعۡزُولُونَ
Open ayah 26:212እነርሱ (የመላእክትን ንግግር) ከመስማት ተከለከሉ ናቸው፡፡
فَلَا تَدۡعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُعَذَّبِينَ
Open ayah 26:213ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፤ ከሚቀጡት ትኾናለህና፡፡
وَأَنذِرۡ عَشِيرَتَكَ ٱلۡأَقۡرَبِينَ
Open ayah 26:214ቅርቦች ዘመዶችህንም አስጠንቅቅ፡፡
وَٱخۡفِضۡ جَنَاحَكَ لِمَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
Open ayah 26:215ከምእምናንም ለተከተሉህ ሰዎች ክንፍህን ዝቅ አድርግ፤ (ልዝብ ኹን)፡፡
فَإِنۡ عَصَوۡكَ فَقُلۡ إِنِّي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تَعۡمَلُونَ
Open ayah 26:216«እንቢ» ቢሉህም «እኔ ከምትሠሩት ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡
وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱلۡعَزِيزِ ٱلرَّحِيمِ
Open ayah 26:217አሸናፊ አዛኝ በኾነው (ጌታህ) ላይም ተጠጋ፡፡
ٱلَّذِي يَرَىٰكَ حِينَ تَقُومُ
Open ayah 26:218በዚያ ለሶላት በምትቆም ጊዜ በሚያይህ፡፡
وَتَقَلُّبَكَ فِي ٱلسَّٰجِدِينَ
Open ayah 26:219በሰጋጆች ውስጥ መዘዋወርህንም (በሚያየው ጌታህ ላይ ተጠጋ)፡፡
إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
Open ayah 26:220እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡
هَلۡ أُنَبِّئُكُمۡ عَلَىٰ مَن تَنَزَّلُ ٱلشَّيَٰطِينُ
Open ayah 26:221ሰይጣናት በማን ላይ እንደሚወርዱ ልንገራችሁን
تَنَزَّلُ عَلَىٰ كُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٖ
Open ayah 26:222በውሸታም ኀጢአተኛ ሁሉ ላይ ይወርዳሉ፡፡
يُلۡقُونَ ٱلسَّمۡعَ وَأَكۡثَرُهُمۡ كَٰذِبُونَ
Open ayah 26:223የሰሙትን (ወደ ጠንቋዮች) ይጥላሉ፡፡ አብዛኞቻቸውም ውሸታሞች ናቸው፡፡
وَٱلشُّعَرَآءُ يَتَّبِعُهُمُ ٱلۡغَاوُۥنَ
Open ayah 26:224ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎቹ ይከተሉዋቸዋል፡፡
أَلَمۡ تَرَ أَنَّهُمۡ فِي كُلِّ وَادٖ يَهِيمُونَ
Open ayah 26:225እነርሱ በ(ንግግር) ሸለቆ ሁሉ የሚዋልሉ መኾናቸውን አታይምን
وَأَنَّهُمۡ يَقُولُونَ مَا لَا يَفۡعَلُونَ
Open ayah 26:226እነሱም የማይሠሩትን ነገር የሚናገሩ መኾናቸውን (አታይምን)፤
إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَذَكَرُواْ ٱللَّهَ كَثِيرٗا وَٱنتَصَرُواْ مِنۢ بَعۡدِ مَا ظُلِمُواْۗ وَسَيَعۡلَمُ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ أَيَّ مُنقَلَبٖ يَنقَلِبُونَ
Open ayah 26:227እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ አላህንም በብዛት ያወሱ ከተበደሉም በኋላ (በቅኔ) የተከላከሉ ሲቀሩ፤ (እነርሱ አይወቀሱም)፡፡ እነዚያም የበደሉ (ከሞቱ በኋላ) እንዴት ያለን መመለስ እንደሚመለሱ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡