الصافات
As-Saaffaat
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
وَٱلصَّٰٓفَّٰتِ صَفّٗا
Open ayah 37:1መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡
فَٱلزَّٰجِرَٰتِ زَجۡرٗا
Open ayah 37:2መገሠጽንም በሚገሥጹት፤
فَٱلتَّٰلِيَٰتِ ذِكۡرًا
Open ayah 37:3ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡
إِنَّ إِلَٰهَكُمۡ لَوَٰحِدٞ
Open ayah 37:4አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡
رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا وَرَبُّ ٱلۡمَشَٰرِقِ
Open ayah 37:5የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡
إِنَّا زَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنۡيَا بِزِينَةٍ ٱلۡكَوَاكِبِ
Open ayah 37:6እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡
وَحِفۡظٗا مِّن كُلِّ شَيۡطَٰنٖ مَّارِدٖ
Open ayah 37:7አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡
لَّا يَسَّمَّعُونَ إِلَى ٱلۡمَلَإِ ٱلۡأَعۡلَىٰ وَيُقۡذَفُونَ مِن كُلِّ جَانِبٖ
Open ayah 37:8ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡
دُحُورٗاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٞ وَاصِبٌ
Open ayah 37:9የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡
إِلَّا مَنۡ خَطِفَ ٱلۡخَطۡفَةَ فَأَتۡبَعَهُۥ شِهَابٞ ثَاقِبٞ
Open ayah 37:10ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡
فَٱسۡتَفۡتِهِمۡ أَهُمۡ أَشَدُّ خَلۡقًا أَم مَّنۡ خَلَقۡنَآۚ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّن طِينٖ لَّازِبِۭ
Open ayah 37:11ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡
بَلۡ عَجِبۡتَ وَيَسۡخَرُونَ
Open ayah 37:12ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡
وَإِذَا ذُكِّرُواْ لَا يَذۡكُرُونَ
Open ayah 37:13በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡
وَإِذَا رَأَوۡاْ ءَايَةٗ يَسۡتَسۡخِرُونَ
Open ayah 37:14ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡
وَقَالُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٌ
Open ayah 37:15ይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ
Open ayah 37:16«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?
أَوَءَابَآؤُنَا ٱلۡأَوَّلُونَ
Open ayah 37:17«የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡
قُلۡ نَعَمۡ وَأَنتُمۡ دَٰخِرُونَ
Open ayah 37:18«አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡
فَإِنَّمَا هِيَ زَجۡرَةٞ وَٰحِدَةٞ فَإِذَا هُمۡ يَنظُرُونَ
Open ayah 37:19እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡
وَقَالُواْ يَٰوَيۡلَنَا هَٰذَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ
Open ayah 37:20«ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡
هَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِ ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ
Open ayah 37:21«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡
۞ٱحۡشُرُواْ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ وَأَزۡوَٰجَهُمۡ وَمَا كَانُواْ يَعۡبُدُونَ
Open ayah 37:22(ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡
مِن دُونِ ٱللَّهِ فَٱهۡدُوهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلۡجَحِيمِ
Open ayah 37:23«ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡
وَقِفُوهُمۡۖ إِنَّهُم مَّسۡـُٔولُونَ
Open ayah 37:24«አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡
مَا لَكُمۡ لَا تَنَاصَرُونَ
Open ayah 37:25(ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡
بَلۡ هُمُ ٱلۡيَوۡمَ مُسۡتَسۡلِمُونَ
Open ayah 37:26በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡
وَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ
Open ayah 37:27የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡
قَالُوٓاْ إِنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَأۡتُونَنَا عَنِ ٱلۡيَمِينِ
Open ayah 37:28(ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡
قَالُواْ بَل لَّمۡ تَكُونُواْ مُؤۡمِنِينَ
Open ayah 37:29(አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡
وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيۡكُم مِّن سُلۡطَٰنِۭۖ بَلۡ كُنتُمۡ قَوۡمٗا طَٰغِينَ
Open ayah 37:30«ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡
فَحَقَّ عَلَيۡنَا قَوۡلُ رَبِّنَآۖ إِنَّا لَذَآئِقُونَ
Open ayah 37:31«በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡
فَأَغۡوَيۡنَٰكُمۡ إِنَّا كُنَّا غَٰوِينَ
Open ayah 37:32«ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡
فَإِنَّهُمۡ يَوۡمَئِذٖ فِي ٱلۡعَذَابِ مُشۡتَرِكُونَ
Open ayah 37:33ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸው፡፡
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَفۡعَلُ بِٱلۡمُجۡرِمِينَ
Open ayah 37:34እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡
إِنَّهُمۡ كَانُوٓاْ إِذَا قِيلَ لَهُمۡ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ يَسۡتَكۡبِرُونَ
Open ayah 37:35እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡
وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوٓاْ ءَالِهَتِنَا لِشَاعِرٖ مَّجۡنُونِۭ
Open ayah 37:36እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡
بَلۡ جَآءَ بِٱلۡحَقِّ وَصَدَّقَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 37:37አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡
إِنَّكُمۡ لَذَآئِقُواْ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡأَلِيمِ
Open ayah 37:38እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡
وَمَا تُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
Open ayah 37:39ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
Open ayah 37:40ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡
أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ رِزۡقٞ مَّعۡلُومٞ
Open ayah 37:41እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡
فَوَٰكِهُ وَهُم مُّكۡرَمُونَ
Open ayah 37:42ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤
فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
Open ayah 37:43በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡
عَلَىٰ سُرُرٖ مُّتَقَٰبِلِينَ
Open ayah 37:44ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡
يُطَافُ عَلَيۡهِم بِكَأۡسٖ مِّن مَّعِينِۭ
Open ayah 37:45ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡
بَيۡضَآءَ لَذَّةٖ لِّلشَّٰرِبِينَ
Open ayah 37:46ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡
لَا فِيهَا غَوۡلٞ وَلَا هُمۡ عَنۡهَا يُنزَفُونَ
Open ayah 37:47በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡
وَعِندَهُمۡ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ عِينٞ
Open ayah 37:48እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡
كَأَنَّهُنَّ بَيۡضٞ مَّكۡنُونٞ
Open ayah 37:49እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡
فَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ
Open ayah 37:50የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡
قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٞ
Open ayah 37:51ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡
يَقُولُ أَءِنَّكَ لَمِنَ ٱلۡمُصَدِّقِينَ
Open ayah 37:52«በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡
أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَدِينُونَ
Open ayah 37:53«በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡
قَالَ هَلۡ أَنتُم مُّطَّلِعُونَ
Open ayah 37:54እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡
فَٱطَّلَعَ فَرَءَاهُ فِي سَوَآءِ ٱلۡجَحِيمِ
Open ayah 37:55ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡
قَالَ تَٱللَّهِ إِن كِدتَّ لَتُرۡدِينِ
Open ayah 37:56ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡
وَلَوۡلَا نِعۡمَةُ رَبِّي لَكُنتُ مِنَ ٱلۡمُحۡضَرِينَ
Open ayah 37:57«የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡»
أَفَمَا نَحۡنُ بِمَيِّتِينَ
Open ayah 37:58(የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን?
إِلَّا مَوۡتَتَنَا ٱلۡأُولَىٰ وَمَا نَحۡنُ بِمُعَذَّبِينَ
Open ayah 37:59«የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ
Open ayah 37:60ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
لِمِثۡلِ هَٰذَا فَلۡيَعۡمَلِ ٱلۡعَٰمِلُونَ
Open ayah 37:61ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡
أَذَٰلِكَ خَيۡرٞ نُّزُلًا أَمۡ شَجَرَةُ ٱلزَّقُّومِ
Open ayah 37:62በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?
إِنَّا جَعَلۡنَٰهَا فِتۡنَةٗ لِّلظَّٰلِمِينَ
Open ayah 37:63እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡
إِنَّهَا شَجَرَةٞ تَخۡرُجُ فِيٓ أَصۡلِ ٱلۡجَحِيمِ
Open ayah 37:64እርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡
طَلۡعُهَا كَأَنَّهُۥ رُءُوسُ ٱلشَّيَٰطِينِ
Open ayah 37:65እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡
فَإِنَّهُمۡ لَأٓكِلُونَ مِنۡهَا فَمَالِـُٔونَ مِنۡهَا ٱلۡبُطُونَ
Open ayah 37:66እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡
ثُمَّ إِنَّ لَهُمۡ عَلَيۡهَا لَشَوۡبٗا مِّنۡ حَمِيمٖ
Open ayah 37:67ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡
ثُمَّ إِنَّ مَرۡجِعَهُمۡ لَإِلَى ٱلۡجَحِيمِ
Open ayah 37:68ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡
إِنَّهُمۡ أَلۡفَوۡاْ ءَابَآءَهُمۡ ضَآلِّينَ
Open ayah 37:69እነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡
فَهُمۡ عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِمۡ يُهۡرَعُونَ
Open ayah 37:70እነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡
وَلَقَدۡ ضَلَّ قَبۡلَهُمۡ أَكۡثَرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
Open ayah 37:71ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا فِيهِم مُّنذِرِينَ
Open ayah 37:72በውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡
فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُنذَرِينَ
Open ayah 37:73የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
Open ayah 37:74ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡
وَلَقَدۡ نَادَىٰنَا نُوحٞ فَلَنِعۡمَ ٱلۡمُجِيبُونَ
Open ayah 37:75ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን!
وَنَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥ مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ
Open ayah 37:76እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡
وَجَعَلۡنَا ذُرِّيَّتَهُۥ هُمُ ٱلۡبَاقِينَ
Open ayah 37:77ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤
وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ
Open ayah 37:78በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡
سَلَٰمٌ عَلَىٰ نُوحٖ فِي ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 37:79«በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡»
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
Open ayah 37:80እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
Open ayah 37:81እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡
ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ
Open ayah 37:82ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡
۞وَإِنَّ مِن شِيعَتِهِۦ لَإِبۡرَٰهِيمَ
Open ayah 37:83ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡
إِذۡ جَآءَ رَبَّهُۥ بِقَلۡبٖ سَلِيمٍ
Open ayah 37:84ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡
إِذۡ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦ مَاذَا تَعۡبُدُونَ
Open ayah 37:85«ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡
أَئِفۡكًا ءَالِهَةٗ دُونَ ٱللَّهِ تُرِيدُونَ
Open ayah 37:86«ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?
فَمَا ظَنُّكُم بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 37:87«በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?» አለ፡፡
فَنَظَرَ نَظۡرَةٗ فِي ٱلنُّجُومِ
Open ayah 37:88በከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡
فَقَالَ إِنِّي سَقِيمٞ
Open ayah 37:89«እኔ በሽተኛ ነኝም» አለ፡፡
فَتَوَلَّوۡاْ عَنۡهُ مُدۡبِرِينَ
Open ayah 37:90ከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡
فَرَاغَ إِلَىٰٓ ءَالِهَتِهِمۡ فَقَالَ أَلَا تَأۡكُلُونَ
Open ayah 37:91ወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- «አትበሉምን?»
مَا لَكُمۡ لَا تَنطِقُونَ
Open ayah 37:92«የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?»
فَرَاغَ عَلَيۡهِمۡ ضَرۡبَۢا بِٱلۡيَمِينِ
Open ayah 37:93በኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡
فَأَقۡبَلُوٓاْ إِلَيۡهِ يَزِفُّونَ
Open ayah 37:94ወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡
قَالَ أَتَعۡبُدُونَ مَا تَنۡحِتُونَ
Open ayah 37:95አላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?»
وَٱللَّهُ خَلَقَكُمۡ وَمَا تَعۡمَلُونَ
Open ayah 37:96«አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡»
قَالُواْ ٱبۡنُواْ لَهُۥ بُنۡيَٰنٗا فَأَلۡقُوهُ فِي ٱلۡجَحِيمِ
Open ayah 37:97«ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ፡፡
فَأَرَادُواْ بِهِۦ كَيۡدٗا فَجَعَلۡنَٰهُمُ ٱلۡأَسۡفَلِينَ
Open ayah 37:98በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡
وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَىٰ رَبِّي سَيَهۡدِينِ
Open ayah 37:99አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡»
رَبِّ هَبۡ لِي مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
Open ayah 37:100ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡
فَبَشَّرۡنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٖ
Open ayah 37:101ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡
فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعۡيَ قَالَ يَٰبُنَيَّ إِنِّيٓ أَرَىٰ فِي ٱلۡمَنَامِ أَنِّيٓ أَذۡبَحُكَ فَٱنظُرۡ مَاذَا تَرَىٰۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفۡعَلۡ مَا تُؤۡمَرُۖ سَتَجِدُنِيٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ
Open ayah 37:102ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡
فَلَمَّآ أَسۡلَمَا وَتَلَّهُۥ لِلۡجَبِينِ
Open ayah 37:103ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡
وَنَٰدَيۡنَٰهُ أَن يَٰٓإِبۡرَٰهِيمُ
Open ayah 37:104ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ!
قَدۡ صَدَّقۡتَ ٱلرُّءۡيَآۚ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
Open ayah 37:105ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡبَلَٰٓؤُاْ ٱلۡمُبِينُ
Open ayah 37:106ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡
وَفَدَيۡنَٰهُ بِذِبۡحٍ عَظِيمٖ
Open ayah 37:107በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡
وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ
Open ayah 37:108በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡
سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ
Open ayah 37:109ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡
كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
Open ayah 37:110እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
Open ayah 37:111እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡
وَبَشَّرۡنَٰهُ بِإِسۡحَٰقَ نَبِيّٗا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
Open ayah 37:112በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡
وَبَٰرَكۡنَا عَلَيۡهِ وَعَلَىٰٓ إِسۡحَٰقَۚ وَمِن ذُرِّيَّتِهِمَا مُحۡسِنٞ وَظَالِمٞ لِّنَفۡسِهِۦ مُبِينٞ
Open ayah 37:113በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡
وَلَقَدۡ مَنَنَّا عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ
Open ayah 37:114በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡
وَنَجَّيۡنَٰهُمَا وَقَوۡمَهُمَا مِنَ ٱلۡكَرۡبِ ٱلۡعَظِيمِ
Open ayah 37:115እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡
وَنَصَرۡنَٰهُمۡ فَكَانُواْ هُمُ ٱلۡغَٰلِبِينَ
Open ayah 37:116ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡
وَءَاتَيۡنَٰهُمَا ٱلۡكِتَٰبَ ٱلۡمُسۡتَبِينَ
Open ayah 37:117በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡
وَهَدَيۡنَٰهُمَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ
Open ayah 37:118ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡
وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِمَا فِي ٱلۡأٓخِرِينَ
Open ayah 37:119በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡
سَلَٰمٌ عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ
Open ayah 37:120ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
Open ayah 37:121እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
إِنَّهُمَا مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
Open ayah 37:122ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡
وَإِنَّ إِلۡيَاسَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 37:123ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِۦٓ أَلَا تَتَّقُونَ
Open ayah 37:124ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን?
أَتَدۡعُونَ بَعۡلٗا وَتَذَرُونَ أَحۡسَنَ ٱلۡخَٰلِقِينَ
Open ayah 37:125በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን?
ٱللَّهَ رَبَّكُمۡ وَرَبَّ ءَابَآئِكُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ
Open ayah 37:126አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን)?
فَكَذَّبُوهُ فَإِنَّهُمۡ لَمُحۡضَرُونَ
Open ayah 37:127አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
Open ayah 37:128ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡
وَتَرَكۡنَا عَلَيۡهِ فِي ٱلۡأٓخِرِينَ
Open ayah 37:129በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡
سَلَٰمٌ عَلَىٰٓ إِلۡ يَاسِينَ
Open ayah 37:130ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡمُحۡسِنِينَ
Open ayah 37:131እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
إِنَّهُۥ مِنۡ عِبَادِنَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
Open ayah 37:132እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡
وَإِنَّ لُوطٗا لَّمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 37:133ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
إِذۡ نَجَّيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ
Open ayah 37:134እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡
إِلَّا عَجُوزٗا فِي ٱلۡغَٰبِرِينَ
Open ayah 37:135(በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡
ثُمَّ دَمَّرۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ
Open ayah 37:136ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡
وَإِنَّكُمۡ لَتَمُرُّونَ عَلَيۡهِم مُّصۡبِحِينَ
Open ayah 37:137እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡
وَبِٱلَّيۡلِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ
Open ayah 37:138በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን?
وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 37:139ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
إِذۡ أَبَقَ إِلَى ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ
Open ayah 37:140ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
فَسَاهَمَ فَكَانَ مِنَ ٱلۡمُدۡحَضِينَ
Open ayah 37:141ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡
فَٱلۡتَقَمَهُ ٱلۡحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٞ
Open ayah 37:142እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡
فَلَوۡلَآ أَنَّهُۥ كَانَ مِنَ ٱلۡمُسَبِّحِينَ
Open ayah 37:143እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤
لَلَبِثَ فِي بَطۡنِهِۦٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ
Open ayah 37:144እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡
۞فَنَبَذۡنَٰهُ بِٱلۡعَرَآءِ وَهُوَ سَقِيمٞ
Open ayah 37:145እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡
وَأَنۢبَتۡنَا عَلَيۡهِ شَجَرَةٗ مِّن يَقۡطِينٖ
Open ayah 37:146በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡
وَأَرۡسَلۡنَٰهُ إِلَىٰ مِاْئَةِ أَلۡفٍ أَوۡ يَزِيدُونَ
Open ayah 37:147ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡
فَـَٔامَنُواْ فَمَتَّعۡنَٰهُمۡ إِلَىٰ حِينٖ
Open ayah 37:148አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡
فَٱسۡتَفۡتِهِمۡ أَلِرَبِّكَ ٱلۡبَنَاتُ وَلَهُمُ ٱلۡبَنُونَ
Open ayah 37:149(የመካን ሰዎች) ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?»
أَمۡ خَلَقۡنَا ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ إِنَٰثٗا وَهُمۡ شَٰهِدُونَ
Open ayah 37:150ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?
أَلَآ إِنَّهُم مِّنۡ إِفۡكِهِمۡ لَيَقُولُونَ
Open ayah 37:151ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡-
وَلَدَ ٱللَّهُ وَإِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ
Open ayah 37:152«አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡
أَصۡطَفَى ٱلۡبَنَاتِ عَلَى ٱلۡبَنِينَ
Open ayah 37:153በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን?
مَا لَكُمۡ كَيۡفَ تَحۡكُمُونَ
Open ayah 37:154ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!
أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
Open ayah 37:155አትገነዘቡምን?
أَمۡ لَكُمۡ سُلۡطَٰنٞ مُّبِينٞ
Open ayah 37:156ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን?
فَأۡتُواْ بِكِتَٰبِكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
Open ayah 37:157«እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)፡፡
وَجَعَلُواْ بَيۡنَهُۥ وَبَيۡنَ ٱلۡجِنَّةِ نَسَبٗاۚ وَلَقَدۡ عَلِمَتِ ٱلۡجِنَّةُ إِنَّهُمۡ لَمُحۡضَرُونَ
Open ayah 37:158በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡
سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ
Open ayah 37:159አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡
إِلَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
Open ayah 37:160ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡
فَإِنَّكُمۡ وَمَا تَعۡبُدُونَ
Open ayah 37:161እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤
مَآ أَنتُمۡ عَلَيۡهِ بِفَٰتِنِينَ
Open ayah 37:162በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡
إِلَّا مَنۡ هُوَ صَالِ ٱلۡجَحِيمِ
Open ayah 37:163ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡
وَمَا مِنَّآ إِلَّا لَهُۥ مَقَامٞ مَّعۡلُومٞ
Open ayah 37:164(ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡
وَإِنَّا لَنَحۡنُ ٱلصَّآفُّونَ
Open ayah 37:165እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡
وَإِنَّا لَنَحۡنُ ٱلۡمُسَبِّحُونَ
Open ayah 37:166እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡
وَإِن كَانُواْ لَيَقُولُونَ
Open ayah 37:167እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡-
لَوۡ أَنَّ عِندَنَا ذِكۡرٗا مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ
Open ayah 37:168«ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤
لَكُنَّا عِبَادَ ٱللَّهِ ٱلۡمُخۡلَصِينَ
Open ayah 37:169«የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡»
فَكَفَرُواْ بِهِۦۖ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ
Open ayah 37:170ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
وَلَقَدۡ سَبَقَتۡ كَلِمَتُنَا لِعِبَادِنَا ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 37:171(የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡
إِنَّهُمۡ لَهُمُ ٱلۡمَنصُورُونَ
Open ayah 37:172እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
وَإِنَّ جُندَنَا لَهُمُ ٱلۡغَٰلِبُونَ
Open ayah 37:173ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
فَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِينٖ
Open ayah 37:174ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡
وَأَبۡصِرۡهُمۡ فَسَوۡفَ يُبۡصِرُونَ
Open ayah 37:175እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡
أَفَبِعَذَابِنَا يَسۡتَعۡجِلُونَ
Open ayah 37:176በቅጣታችንም ያቻኩላሉን?
فَإِذَا نَزَلَ بِسَاحَتِهِمۡ فَسَآءَ صَبَاحُ ٱلۡمُنذَرِينَ
Open ayah 37:177በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!
وَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِينٖ
Open ayah 37:178እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡
وَأَبۡصِرۡ فَسَوۡفَ يُبۡصِرُونَ
Open ayah 37:179ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡
سُبۡحَٰنَ رَبِّكَ رَبِّ ٱلۡعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ
Open ayah 37:180የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡
وَسَلَٰمٌ عَلَى ٱلۡمُرۡسَلِينَ
Open ayah 37:181በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤
وَٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 37:182ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡