الواقعة
Al-Waaqia
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
إِذَا وَقَعَتِ ٱلۡوَاقِعَةُ
Open ayah 56:1መከራይቱ በወደቀች ጊዜ፡፡
لَيۡسَ لِوَقۡعَتِهَا كَاذِبَةٌ
Open ayah 56:2ለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም፡፡
خَافِضَةٞ رَّافِعَةٌ
Open ayah 56:3ዝቅ አድራጊና ከፍ አድራጊ ናት፡፡
إِذَا رُجَّتِ ٱلۡأَرۡضُ رَجّٗا
Open ayah 56:4ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ፡፡
وَبُسَّتِ ٱلۡجِبَالُ بَسّٗا
Open ayah 56:5ተራራዎችም መፍፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በኾኑ ጊዜ)፡፡
فَكَانَتۡ هَبَآءٗ مُّنۢبَثّٗا
Open ayah 56:6የተበተነ ብናኝ በኾኑም ጊዜ
وَكُنتُمۡ أَزۡوَٰجٗا ثَلَٰثَةٗ
Open ayah 56:7ሦስት ዓይነቶችም በኾናችሁ ጊዜ (ታዋርዳለች፤ ታነሳለችም)፡፡
فَأَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ
Open ayah 56:8የቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ
Open ayah 56:9የግራ ጓዶችም ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
وَٱلسَّٰبِقُونَ ٱلسَّٰبِقُونَ
Open ayah 56:10(ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው፡፡
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلۡمُقَرَّبُونَ
Open ayah 56:11እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡
فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ
Open ayah 56:12በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲኾኑ፡፡
ثُلَّةٞ مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ
Open ayah 56:13ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
وَقَلِيلٞ مِّنَ ٱلۡأٓخِرِينَ
Open ayah 56:14ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡
عَلَىٰ سُرُرٖ مَّوۡضُونَةٖ
Open ayah 56:15በተታቱ አልጋዎች ላይ ይኾናሉ፡፡
مُّتَّكِـِٔينَ عَلَيۡهَا مُتَقَٰبِلِينَ
Open ayah 56:16በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲኾኑ፡፡
يَطُوفُ عَلَيۡهِمۡ وِلۡدَٰنٞ مُّخَلَّدُونَ
Open ayah 56:17በእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡
بِأَكۡوَابٖ وَأَبَارِيقَ وَكَأۡسٖ مِّن مَّعِينٖ
Open ayah 56:18ከጠጅ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ)፡፡
لَّا يُصَدَّعُونَ عَنۡهَا وَلَا يُنزِفُونَ
Open ayah 56:19ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡
وَفَٰكِهَةٖ مِّمَّا يَتَخَيَّرُونَ
Open ayah 56:20ከሚመርጡትም ዓይነት በእሸቶች፡፡
وَلَحۡمِ طَيۡرٖ مِّمَّا يَشۡتَهُونَ
Open ayah 56:21ከሚሹትም በኾነ የበራሪ ሥጋ (ይዞሩባቸዋል)፡፡
وَحُورٌ عِينٞ
Open ayah 56:22ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡
كَأَمۡثَٰلِ ٱللُّؤۡلُوِٕ ٱلۡمَكۡنُونِ
Open ayah 56:23ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡
جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
Open ayah 56:24በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡
لَا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوٗا وَلَا تَأۡثِيمًا
Open ayah 56:25በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም፡፡
إِلَّا قِيلٗا سَلَٰمٗا سَلَٰمٗا
Open ayah 56:26ግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡
وَأَصۡحَٰبُ ٱلۡيَمِينِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلۡيَمِينِ
Open ayah 56:27የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች!
فِي سِدۡرٖ مَّخۡضُودٖ
Open ayah 56:28በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው፡፡
وَطَلۡحٖ مَّنضُودٖ
Open ayah 56:29(ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም፡፡
وَظِلّٖ مَّمۡدُودٖ
Open ayah 56:30በተዘረጋ ጥላ ሥርም፡፡
وَمَآءٖ مَّسۡكُوبٖ
Open ayah 56:31በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም፡፡
وَفَٰكِهَةٖ كَثِيرَةٖ
Open ayah 56:32ብዙ (ዓይነት) በኾኑ ፍራፍሬዎችም፡፡
لَّا مَقۡطُوعَةٖ وَلَا مَمۡنُوعَةٖ
Open ayah 56:33የማትቋረጥም የማትከለከልም የኾነች፡፡
وَفُرُشٖ مَّرۡفُوعَةٍ
Open ayah 56:34ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም (ሴቶችም መካከል)፡፡
إِنَّآ أَنشَأۡنَٰهُنَّ إِنشَآءٗ
Open ayah 56:35እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለእነርሱ) ፈጠርናቸው፡፡
فَجَعَلۡنَٰهُنَّ أَبۡكَارًا
Open ayah 56:36ደናግሎችም አደረግናቸው፡፡
عُرُبًا أَتۡرَابٗا
Open ayah 56:37ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)፡፡
لِّأَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ
Open ayah 56:38ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)፡፡
ثُلَّةٞ مِّنَ ٱلۡأَوَّلِينَ
Open ayah 56:39ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
وَثُلَّةٞ مِّنَ ٱلۡأٓخِرِينَ
Open ayah 56:40ከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
وَأَصۡحَٰبُ ٱلشِّمَالِ مَآ أَصۡحَٰبُ ٱلشِّمَالِ
Open ayah 56:41የግራ ጓደኞችም ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው፡፡
فِي سَمُومٖ وَحَمِيمٖ
Open ayah 56:42በመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው፡፡
وَظِلّٖ مِّن يَحۡمُومٖ
Open ayah 56:43ከጥቁር ጭስም በኾነ ጥላ ውስጥ፡፡
لَّا بَارِدٖ وَلَا كَرِيمٍ
Open ayah 56:44ቀዝቃዛም መልካምም ያልኾነ፡፡
إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَبۡلَ ذَٰلِكَ مُتۡرَفِينَ
Open ayah 56:45እነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና፡፡
وَكَانُواْ يُصِرُّونَ عَلَى ٱلۡحِنثِ ٱلۡعَظِيمِ
Open ayah 56:46በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና፡፡
وَكَانُواْ يَقُولُونَ أَئِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ
Open ayah 56:47ይሉም ነበሩ፡- «በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን?
أَوَءَابَآؤُنَا ٱلۡأَوَّلُونَ
Open ayah 56:48«የፊተኞቹ አባቶቻችንም?»
قُلۡ إِنَّ ٱلۡأَوَّلِينَ وَٱلۡأٓخِرِينَ
Open ayah 56:49በላቸው፡- «ፊተኞቹም ኋለኞቹም፡፡
لَمَجۡمُوعُونَ إِلَىٰ مِيقَٰتِ يَوۡمٖ مَّعۡلُومٖ
Open ayah 56:50«በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው፡፡
ثُمَّ إِنَّكُمۡ أَيُّهَا ٱلضَّآلُّونَ ٱلۡمُكَذِّبُونَ
Open ayah 56:51«ከዚያም እናንተ ጠማሞች አስተባባዮች ሆይ!
لَأٓكِلُونَ مِن شَجَرٖ مِّن زَقُّومٖ
Open ayah 56:52« ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ፡፡
فَمَالِـُٔونَ مِنۡهَا ٱلۡبُطُونَ
Open ayah 56:53«ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ፡፡
فَشَٰرِبُونَ عَلَيۡهِ مِنَ ٱلۡحَمِيمِ
Open ayah 56:54«በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችሁ፡፡
فَشَٰرِبُونَ شُرۡبَ ٱلۡهِيمِ
Open ayah 56:55«የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናችሁ፡፡»
هَٰذَا نُزُلُهُمۡ يَوۡمَ ٱلدِّينِ
Open ayah 56:56ይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው፡፡
نَحۡنُ خَلَقۡنَٰكُمۡ فَلَوۡلَا تُصَدِّقُونَ
Open ayah 56:57እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን?
أَفَرَءَيۡتُم مَّا تُمۡنُونَ
Open ayah 56:58(በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁን?
ءَأَنتُمۡ تَخۡلُقُونَهُۥٓ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡخَٰلِقُونَ
Open ayah 56:59እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን?
نَحۡنُ قَدَّرۡنَا بَيۡنَكُمُ ٱلۡمَوۡتَ وَمَا نَحۡنُ بِمَسۡبُوقِينَ
Open ayah 56:60እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡
عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ أَمۡثَٰلَكُمۡ وَنُنشِئَكُمۡ فِي مَا لَا تَعۡلَمُونَ
Open ayah 56:61ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)፡፡
وَلَقَدۡ عَلِمۡتُمُ ٱلنَّشۡأَةَ ٱلۡأُولَىٰ فَلَوۡلَا تَذَكَّرُونَ
Open ayah 56:62የፊተኛይቱንም አፈጣጠር በእርግጥ ዐውቃችኋል፡፡ አትገነዘቡምን?
أَفَرَءَيۡتُم مَّا تَحۡرُثُونَ
Open ayah 56:63የምትዘሩትንም አያችሁን?
ءَأَنتُمۡ تَزۡرَعُونَهُۥٓ أَمۡ نَحۡنُ ٱلزَّٰرِعُونَ
Open ayah 56:64እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?
لَوۡ نَشَآءُ لَجَعَلۡنَٰهُ حُطَٰمٗا فَظَلۡتُمۡ تَفَكَّهُونَ
Open ayah 56:65ብነሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በኾናችሁ ነበር፡፡
إِنَّا لَمُغۡرَمُونَ
Open ayah 56:66«እኛ በዕዳ ተያዦች ነን፡፡
بَلۡ نَحۡنُ مَحۡرُومُونَ
Open ayah 56:67«በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን» (ትሉ ነበር)፡፡
أَفَرَءَيۡتُمُ ٱلۡمَآءَ ٱلَّذِي تَشۡرَبُونَ
Open ayah 56:68ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አየችሁን?
ءَأَنتُمۡ أَنزَلۡتُمُوهُ مِنَ ٱلۡمُزۡنِ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡمُنزِلُونَ
Open ayah 56:69እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?
لَوۡ نَشَآءُ جَعَلۡنَٰهُ أُجَاجٗا فَلَوۡلَا تَشۡكُرُونَ
Open ayah 56:70ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን?
أَفَرَءَيۡتُمُ ٱلنَّارَ ٱلَّتِي تُورُونَ
Open ayah 56:71ያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን?
ءَأَنتُمۡ أَنشَأۡتُمۡ شَجَرَتَهَآ أَمۡ نَحۡنُ ٱلۡمُنشِـُٔونَ
Open ayah 56:72እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን?
نَحۡنُ جَعَلۡنَٰهَا تَذۡكِرَةٗ وَمَتَٰعٗا لِّلۡمُقۡوِينَ
Open ayah 56:73እኛ (ለገሀናም) ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት፡፡
فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ
Open ayah 56:74የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡
۞فَلَآ أُقۡسِمُ بِمَوَٰقِعِ ٱلنُّجُومِ
Open ayah 56:75በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ፡፡
وَإِنَّهُۥ لَقَسَمٞ لَّوۡ تَعۡلَمُونَ عَظِيمٌ
Open ayah 56:76እርሱም ብታወቁ ታላቅ መሓላ ነው፡፡
إِنَّهُۥ لَقُرۡءَانٞ كَرِيمٞ
Open ayah 56:77እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
فِي كِتَٰبٖ مَّكۡنُونٖ
Open ayah 56:78በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡
لَّا يَمَسُّهُۥٓ إِلَّا ٱلۡمُطَهَّرُونَ
Open ayah 56:79የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡
تَنزِيلٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 56:80ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡
أَفَبِهَٰذَا ٱلۡحَدِيثِ أَنتُم مُّدۡهِنُونَ
Open ayah 56:81በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን?
وَتَجۡعَلُونَ رِزۡقَكُمۡ أَنَّكُمۡ تُكَذِّبُونَ
Open ayah 56:82ሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን?
فَلَوۡلَآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلۡحُلۡقُومَ
Open ayah 56:83(ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡
وَأَنتُمۡ حِينَئِذٖ تَنظُرُونَ
Open ayah 56:84እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትኾኑ፡፡
وَنَحۡنُ أَقۡرَبُ إِلَيۡهِ مِنكُمۡ وَلَٰكِن لَّا تُبۡصِرُونَ
Open ayah 56:85እኛም ግን አታዩም እንጅ ከእናንተ ይልቅ ወደእርሱ የቀረብን ስንኾን፡፡
فَلَوۡلَآ إِن كُنتُمۡ غَيۡرَ مَدِينِينَ
Open ayah 56:86የማትዳኙም ከኾናችሁ፡፡
تَرۡجِعُونَهَآ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
Open ayah 56:87እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም፡፡
فَأَمَّآ إِن كَانَ مِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ
Open ayah 56:88(ሟቹ) ከባለሟሎቹ ቢኾንማ፡፡
فَرَوۡحٞ وَرَيۡحَانٞ وَجَنَّتُ نَعِيمٖ
Open ayah 56:89(ለእርሱ) ዕረፍት፣ መልካም ሲሳይም፣ የመጠቀሚያ ገነትም አልለው፡፡
وَأَمَّآ إِن كَانَ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ
Open ayah 56:90ከቀኝ ጓዶችም ቢኾንማ፡፡
فَسَلَٰمٞ لَّكَ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلۡيَمِينِ
Open ayah 56:91ከቀኝ ጓዶች ስለ ኾንክ ላንተ ሰላም አልለህ (ይባላል)፡፡
وَأَمَّآ إِن كَانَ مِنَ ٱلۡمُكَذِّبِينَ ٱلضَّآلِّينَ
Open ayah 56:92ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢኾንማ፡፡
فَنُزُلٞ مِّنۡ حَمِيمٖ
Open ayah 56:93ከፈላ ውሃ የኾነ መስተንግዶ አልለው፡፡
وَتَصۡلِيَةُ جَحِيمٍ
Open ayah 56:94በገሀነም መቃጠልም (አልለው)፡፡
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ حَقُّ ٱلۡيَقِينِ
Open ayah 56:95ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡
فَسَبِّحۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلۡعَظِيمِ
Open ayah 56:96የታላቁንም ጌታህን ስም አወድስ፡፡