المطففين
Al-Mutaffifin
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
وَيۡلٞ لِّلۡمُطَفِّفِينَ
Open ayah 83:1ለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡
ٱلَّذِينَ إِذَا ٱكۡتَالُواْ عَلَى ٱلنَّاسِ يَسۡتَوۡفُونَ
Open ayah 83:2ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፡፡
وَإِذَا كَالُوهُمۡ أَو وَّزَنُوهُمۡ يُخۡسِرُونَ
Open ayah 83:3ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡
أَلَا يَظُنُّ أُوْلَٰٓئِكَ أَنَّهُم مَّبۡعُوثُونَ
Open ayah 83:4እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መኾናቸውን አያውቁምን?
لِيَوۡمٍ عَظِيمٖ
Open ayah 83:5በታላቁ ቀን፡፡
يَوۡمَ يَقُومُ ٱلنَّاسُ لِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
Open ayah 83:6ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ)፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መኾናቸውን)፡፡
كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٖ
Open ayah 83:7በእውነት የከሓዲዎቹ (የሰላቢዎቹ) መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፡፡
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا سِجِّينٞ
Open ayah 83:8ሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
كِتَٰبٞ مَّرۡقُومٞ
Open ayah 83:9የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡
وَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ
Open ayah 83:10ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
ٱلَّذِينَ يُكَذِّبُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ
Open ayah 83:11ለእነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት፡፡
وَمَا يُكَذِّبُ بِهِۦٓ إِلَّا كُلُّ مُعۡتَدٍ أَثِيمٍ
Open ayah 83:12በእርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጅ ሌላ አያስተባብልም፡፡
إِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا قَالَ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ
Open ayah 83:13አንቀጾቻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡
كَلَّاۖ بَلۡۜ رَانَ عَلَىٰ قُلُوبِهِم مَّا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ
Open ayah 83:14ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡
كَلَّآ إِنَّهُمۡ عَن رَّبِّهِمۡ يَوۡمَئِذٖ لَّمَحۡجُوبُونَ
Open ayah 83:15ይከልከሉ፤ እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው (ማየት) ተጋራጆች ናቸው፡፡
ثُمَّ إِنَّهُمۡ لَصَالُواْ ٱلۡجَحِيمِ
Open ayah 83:16ከዚያም እነርሱ በእርግጥ ገሀነምን ገቢዎች ናቸው፡፡
ثُمَّ يُقَالُ هَٰذَا ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ
Open ayah 83:17ከዚያም «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡
كَلَّآ إِنَّ كِتَٰبَ ٱلۡأَبۡرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ
Open ayah 83:18በእውነቱ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው፡፡
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا عِلِّيُّونَ
Open ayah 83:19ዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
كِتَٰبٞ مَّرۡقُومٞ
Open ayah 83:20የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡
يَشۡهَدُهُ ٱلۡمُقَرَّبُونَ
Open ayah 83:21ባለሟልዎቹ ይጣዱታል፡፡
إِنَّ ٱلۡأَبۡرَارَ لَفِي نَعِيمٍ
Open ayah 83:22እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡
عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ
Open ayah 83:23በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው ይመለከታሉ፡፡
تَعۡرِفُ فِي وُجُوهِهِمۡ نَضۡرَةَ ٱلنَّعِيمِ
Open ayah 83:24በፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ታውቃለህ፡፡
يُسۡقَوۡنَ مِن رَّحِيقٖ مَّخۡتُومٍ
Open ayah 83:25ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ፡፡
خِتَٰمُهُۥ مِسۡكٞۚ وَفِي ذَٰلِكَ فَلۡيَتَنَافَسِ ٱلۡمُتَنَٰفِسُونَ
Open ayah 83:26ማተሚያው ምስክ ከኾነ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ፡፡
وَمِزَاجُهُۥ مِن تَسۡنِيمٍ
Open ayah 83:27መበረዣውም ከተስኒም ነው፡፡
عَيۡنٗا يَشۡرَبُ بِهَا ٱلۡمُقَرَّبُونَ
Open ayah 83:28ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡
إِنَّ ٱلَّذِينَ أَجۡرَمُواْ كَانُواْ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ يَضۡحَكُونَ
Open ayah 83:29እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡
وَإِذَا مَرُّواْ بِهِمۡ يَتَغَامَزُونَ
Open ayah 83:30በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር፡፡
وَإِذَا ٱنقَلَبُوٓاْ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمُ ٱنقَلَبُواْ فَكِهِينَ
Open ayah 83:31ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር፡፡
وَإِذَا رَأَوۡهُمۡ قَالُوٓاْ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَضَآلُّونَ
Open ayah 83:32ባዩዋቸውም ጊዜ «እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው» ይሉ ነበር፡፡
وَمَآ أُرۡسِلُواْ عَلَيۡهِمۡ حَٰفِظِينَ
Open ayah 83:33በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ፡፡
فَٱلۡيَوۡمَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنَ ٱلۡكُفَّارِ يَضۡحَكُونَ
Open ayah 83:34ዛሬ (በትንሣኤ ቀን) እነዚያ ያመኑት በከሓዲዎቹ ይስቃሉ፡፡
عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ يَنظُرُونَ
Open ayah 83:35በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው የሚመለከቱ ሲኾኑ (ይስቃሉ)፡፡
هَلۡ ثُوِّبَ ٱلۡكُفَّارُ مَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ
Open ayah 83:36ከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)፡፡