الإنفطار
Al-Infitaar
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
إِذَا ٱلسَّمَآءُ ٱنفَطَرَتۡ
Open ayah 82:1ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡكَوَاكِبُ ٱنتَثَرَتۡ
Open ayah 82:2ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡبِحَارُ فُجِّرَتۡ
Open ayah 82:3ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤
وَإِذَا ٱلۡقُبُورُ بُعۡثِرَتۡ
Open ayah 82:4መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤
عَلِمَتۡ نَفۡسٞ مَّا قَدَّمَتۡ وَأَخَّرَتۡ
Open ayah 82:5ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡
يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡإِنسَٰنُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ ٱلۡكَرِيمِ
Open ayah 82:6አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?
ٱلَّذِي خَلَقَكَ فَسَوَّىٰكَ فَعَدَلَكَ
Open ayah 82:7በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡
فِيٓ أَيِّ صُورَةٖ مَّا شَآءَ رَكَّبَكَ
Open ayah 82:8በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡
كَلَّا بَلۡ تُكَذِّبُونَ بِٱلدِّينِ
Open ayah 82:9ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡
وَإِنَّ عَلَيۡكُمۡ لَحَٰفِظِينَ
Open ayah 82:10በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤
كِرَامٗا كَٰتِبِينَ
Open ayah 82:11የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡
يَعۡلَمُونَ مَا تَفۡعَلُونَ
Open ayah 82:12የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡
إِنَّ ٱلۡأَبۡرَارَ لَفِي نَعِيمٖ
Open ayah 82:13እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡
وَإِنَّ ٱلۡفُجَّارَ لَفِي جَحِيمٖ
Open ayah 82:14ከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡
يَصۡلَوۡنَهَا يَوۡمَ ٱلدِّينِ
Open ayah 82:15በፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡
وَمَا هُمۡ عَنۡهَا بِغَآئِبِينَ
Open ayah 82:16እነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ
Open ayah 82:17የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
ثُمَّ مَآ أَدۡرَىٰكَ مَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ
Open ayah 82:18ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
يَوۡمَ لَا تَمۡلِكُ نَفۡسٞ لِّنَفۡسٖ شَيۡـٔٗاۖ وَٱلۡأَمۡرُ يَوۡمَئِذٖ لِّلَّهِ
Open ayah 82:19(እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡