الإنشقاق
Al-Inshiqaaq
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
إِذَا ٱلسَّمَآءُ ٱنشَقَّتۡ
Open ayah 84:1ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤
وَأَذِنَتۡ لِرَبِّهَا وَحُقَّتۡ
Open ayah 84:2ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤
وَإِذَا ٱلۡأَرۡضُ مُدَّتۡ
Open ayah 84:3ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤
وَأَلۡقَتۡ مَا فِيهَا وَتَخَلَّتۡ
Open ayah 84:4በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤
وَأَذِنَتۡ لِرَبِّهَا وَحُقَّتۡ
Open ayah 84:5ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡
يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡإِنسَٰنُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدۡحٗا فَمُلَٰقِيهِ
Open ayah 84:6አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡
فَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ بِيَمِينِهِۦ
Open ayah 84:7መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤
فَسَوۡفَ يُحَاسَبُ حِسَابٗا يَسِيرٗا
Open ayah 84:8በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡
وَيَنقَلِبُ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ مَسۡرُورٗا
Open ayah 84:9ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡
وَأَمَّا مَنۡ أُوتِيَ كِتَٰبَهُۥ وَرَآءَ ظَهۡرِهِۦ
Open ayah 84:10መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤
فَسَوۡفَ يَدۡعُواْ ثُبُورٗا
Open ayah 84:11(ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡
وَيَصۡلَىٰ سَعِيرًا
Open ayah 84:12የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡
إِنَّهُۥ كَانَ فِيٓ أَهۡلِهِۦ مَسۡرُورًا
Open ayah 84:13እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡
إِنَّهُۥ ظَنَّ أَن لَّن يَحُورَ
Open ayah 84:14እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡
بَلَىٰٓۚ إِنَّ رَبَّهُۥ كَانَ بِهِۦ بَصِيرٗا
Open ayah 84:15አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡
فَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلشَّفَقِ
Open ayah 84:16አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡
وَٱلَّيۡلِ وَمَا وَسَقَ
Open ayah 84:17በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤
وَٱلۡقَمَرِ إِذَا ٱتَّسَقَ
Open ayah 84:18በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡
لَتَرۡكَبُنَّ طَبَقًا عَن طَبَقٖ
Open ayah 84:19ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡
فَمَا لَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
Open ayah 84:20የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው?
وَإِذَا قُرِئَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقُرۡءَانُ لَا يَسۡجُدُونَۤ۩
Open ayah 84:21በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?)
بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يُكَذِّبُونَ
Open ayah 84:22በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡
وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا يُوعُونَ
Open ayah 84:23አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡
فَبَشِّرۡهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ
Open ayah 84:24በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡
إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ أَجۡرٌ غَيۡرُ مَمۡنُونِۭ
Open ayah 84:25ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡