البروج
Al-Burooj
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلۡبُرُوجِ
Open ayah 85:1የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡
وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡمَوۡعُودِ
Open ayah 85:2በተቀጠረው ቀንም፤
وَشَاهِدٖ وَمَشۡهُودٖ
Open ayah 85:3በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡
قُتِلَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡأُخۡدُودِ
Open ayah 85:4የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡
ٱلنَّارِ ذَاتِ ٱلۡوَقُودِ
Open ayah 85:5የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡
إِذۡ هُمۡ عَلَيۡهَا قُعُودٞ
Open ayah 85:6እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡
وَهُمۡ عَلَىٰ مَا يَفۡعَلُونَ بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ شُهُودٞ
Open ayah 85:7እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡
وَمَا نَقَمُواْ مِنۡهُمۡ إِلَّآ أَن يُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَمِيدِ
Open ayah 85:8ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡
ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ
Open ayah 85:9በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡
إِنَّ ٱلَّذِينَ فَتَنُواْ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ ثُمَّ لَمۡ يَتُوبُواْ فَلَهُمۡ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمۡ عَذَابُ ٱلۡحَرِيقِ
Open ayah 85:10እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ جَنَّٰتٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡكَبِيرُ
Open ayah 85:11እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
إِنَّ بَطۡشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ
Open ayah 85:12የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡
إِنَّهُۥ هُوَ يُبۡدِئُ وَيُعِيدُ
Open ayah 85:13እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡
وَهُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلۡوَدُودُ
Open ayah 85:14እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡
ذُو ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡمَجِيدُ
Open ayah 85:15የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡
فَعَّالٞ لِّمَا يُرِيدُ
Open ayah 85:16የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡
هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ٱلۡجُنُودِ
Open ayah 85:17የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን?
فِرۡعَوۡنَ وَثَمُودَ
Open ayah 85:18የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡
بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي تَكۡذِيبٖ
Open ayah 85:19በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡
وَٱللَّهُ مِن وَرَآئِهِم مُّحِيطُۢ
Open ayah 85:20አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡
بَلۡ هُوَ قُرۡءَانٞ مَّجِيدٞ
Open ayah 85:21ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
فِي لَوۡحٖ مَّحۡفُوظِۭ
Open ayah 85:22የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡