الطارق
At-Taariq
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
وَٱلسَّمَآءِ وَٱلطَّارِقِ
Open ayah 86:1በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلطَّارِقُ
Open ayah 86:2የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
ٱلنَّجۡمُ ٱلثَّاقِبُ
Open ayah 86:3ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡
إِن كُلُّ نَفۡسٖ لَّمَّا عَلَيۡهَا حَافِظٞ
Open ayah 86:4ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
فَلۡيَنظُرِ ٱلۡإِنسَٰنُ مِمَّ خُلِقَ
Open ayah 86:5ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡
خُلِقَ مِن مَّآءٖ دَافِقٖ
Open ayah 86:6ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡
يَخۡرُجُ مِنۢ بَيۡنِ ٱلصُّلۡبِ وَٱلتَّرَآئِبِ
Open ayah 86:7ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡
إِنَّهُۥ عَلَىٰ رَجۡعِهِۦ لَقَادِرٞ
Open ayah 86:8እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡
يَوۡمَ تُبۡلَى ٱلسَّرَآئِرُ
Open ayah 86:9ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡
فَمَا لَهُۥ مِن قُوَّةٖ وَلَا نَاصِرٖ
Open ayah 86:10ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡
وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلرَّجۡعِ
Open ayah 86:11የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡
وَٱلۡأَرۡضِ ذَاتِ ٱلصَّدۡعِ
Open ayah 86:12(በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤
إِنَّهُۥ لَقَوۡلٞ فَصۡلٞ
Open ayah 86:13እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡
وَمَا هُوَ بِٱلۡهَزۡلِ
Open ayah 86:14እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡
إِنَّهُمۡ يَكِيدُونَ كَيۡدٗا
Open ayah 86:15እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡
وَأَكِيدُ كَيۡدٗا
Open ayah 86:16(እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡
فَمَهِّلِ ٱلۡكَٰفِرِينَ أَمۡهِلۡهُمۡ رُوَيۡدَۢا
Open ayah 86:17ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡