الأعلى
Al-A'laa
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
سَبِّحِ ٱسۡمَ رَبِّكَ ٱلۡأَعۡلَى
Open ayah 87:1ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡
ٱلَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ
Open ayah 87:2የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡
وَٱلَّذِي قَدَّرَ فَهَدَىٰ
Open ayah 87:3የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡
وَٱلَّذِيٓ أَخۡرَجَ ٱلۡمَرۡعَىٰ
Open ayah 87:4የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡
فَجَعَلَهُۥ غُثَآءً أَحۡوَىٰ
Open ayah 87:5(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡
سَنُقۡرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰٓ
Open ayah 87:6(ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡
إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۚ إِنَّهُۥ يَعۡلَمُ ٱلۡجَهۡرَ وَمَا يَخۡفَىٰ
Open ayah 87:7አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡
وَنُيَسِّرُكَ لِلۡيُسۡرَىٰ
Open ayah 87:8ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡
فَذَكِّرۡ إِن نَّفَعَتِ ٱلذِّكۡرَىٰ
Open ayah 87:9ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡
سَيَذَّكَّرُ مَن يَخۡشَىٰ
Open ayah 87:10(አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡
وَيَتَجَنَّبُهَا ٱلۡأَشۡقَى
Open ayah 87:11መናጢውም ይርቃታል፡፡
ٱلَّذِي يَصۡلَى ٱلنَّارَ ٱلۡكُبۡرَىٰ
Open ayah 87:12ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡
ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحۡيَىٰ
Open ayah 87:13ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡
قَدۡ أَفۡلَحَ مَن تَزَكَّىٰ
Open ayah 87:14የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡
وَذَكَرَ ٱسۡمَ رَبِّهِۦ فَصَلَّىٰ
Open ayah 87:15የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡
بَلۡ تُؤۡثِرُونَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا
Open ayah 87:16ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡
وَٱلۡأٓخِرَةُ خَيۡرٞ وَأَبۡقَىٰٓ
Open ayah 87:17መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡
إِنَّ هَٰذَا لَفِي ٱلصُّحُفِ ٱلۡأُولَىٰ
Open ayah 87:18ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡
صُحُفِ إِبۡرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ
Open ayah 87:19በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡