القيامة
Al-Qiyaama
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
لَآ أُقۡسِمُ بِيَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ
Open ayah 75:1(ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡
وَلَآ أُقۡسِمُ بِٱلنَّفۡسِ ٱللَّوَّامَةِ
Open ayah 75:2(ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡
أَيَحۡسَبُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَلَّن نَّجۡمَعَ عِظَامَهُۥ
Open ayah 75:3ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን?
بَلَىٰ قَٰدِرِينَ عَلَىٰٓ أَن نُّسَوِّيَ بَنَانَهُۥ
Open ayah 75:4አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን (እንሰበስባቸዋለን)፡፡
بَلۡ يُرِيدُ ٱلۡإِنسَٰنُ لِيَفۡجُرَ أَمَامَهُۥ
Open ayah 75:5ይልቁንም ሰው በፊቱ ባለው ነገር (በትንሣኤ) ሊያስተባብል ይፈልጋል፡፡
يَسۡـَٔلُ أَيَّانَ يَوۡمُ ٱلۡقِيَٰمَةِ
Open ayah 75:6«የትንሣኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል፡፡
فَإِذَا بَرِقَ ٱلۡبَصَرُ
Open ayah 75:7ዓይንም በዋለለ ጊዜ፡፡
وَخَسَفَ ٱلۡقَمَرُ
Open ayah 75:8ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፡፡
وَجُمِعَ ٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُ
Open ayah 75:9ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፡፡
يَقُولُ ٱلۡإِنسَٰنُ يَوۡمَئِذٍ أَيۡنَ ٱلۡمَفَرُّ
Open ayah 75:10«ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው?» ይላል፡፡
كَلَّا لَا وَزَرَ
Open ayah 75:11ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም፡፡
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡمُسۡتَقَرُّ
Open ayah 75:12በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
يُنَبَّؤُاْ ٱلۡإِنسَٰنُ يَوۡمَئِذِۭ بِمَا قَدَّمَ وَأَخَّرَ
Open ayah 75:13ሰው በዚያ ቀን ባስቀደመውና ባስቆየው ሁሉ ይነገራል፡፡
بَلِ ٱلۡإِنسَٰنُ عَلَىٰ نَفۡسِهِۦ بَصِيرَةٞ
Open ayah 75:14በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡
وَلَوۡ أَلۡقَىٰ مَعَاذِيرَهُۥ
Open ayah 75:15ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣም እንኳ (አይሰማም)፡፡
لَا تُحَرِّكۡ بِهِۦ لِسَانَكَ لِتَعۡجَلَ بِهِۦٓ
Open ayah 75:16በእርሱ (በቁርኣን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ፡፡
إِنَّ عَلَيۡنَا جَمۡعَهُۥ وَقُرۡءَانَهُۥ
Open ayah 75:17(በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡
فَإِذَا قَرَأۡنَٰهُ فَٱتَّبِعۡ قُرۡءَانَهُۥ
Open ayah 75:18ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡
ثُمَّ إِنَّ عَلَيۡنَا بَيَانَهُۥ
Open ayah 75:19ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡
كَلَّا بَلۡ تُحِبُّونَ ٱلۡعَاجِلَةَ
Open ayah 75:20(ከመጣደፍ) ተከልከል፡፡ ይልቁንም (ሰዎች) ፈጣኒቱን (ዓለም) ትወዳላችሁ፡፡
وَتَذَرُونَ ٱلۡأٓخِرَةَ
Open ayah 75:21መጨረሻይቱንም (ዓለም) ትተዋላችሁ፡፡ (አትዘጋጁላትም)፡፡
وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٖ نَّاضِرَةٌ
Open ayah 75:22ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡
إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٞ
Open ayah 75:23ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡
وَوُجُوهٞ يَوۡمَئِذِۭ بَاسِرَةٞ
Open ayah 75:24ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡
تَظُنُّ أَن يُفۡعَلَ بِهَا فَاقِرَةٞ
Open ayah 75:25በርሳቸውም ዐደጋ እንደሚሠራባቸው ያረጋግጣሉ፡፡
كَلَّآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلتَّرَاقِيَ
Open ayah 75:26ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤
وَقِيلَ مَنۡۜ رَاقٖ
Open ayah 75:27«አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡
وَظَنَّ أَنَّهُ ٱلۡفِرَاقُ
Open ayah 75:28(ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡
وَٱلۡتَفَّتِ ٱلسَّاقُ بِٱلسَّاقِ
Open ayah 75:29ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡمَسَاقُ
Open ayah 75:30በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ (ፍርድ) ነው፡፡
فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ
Open ayah 75:31አላመነምም አልሰገደምም፡፡
وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ
Open ayah 75:32ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡
ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ يَتَمَطَّىٰٓ
Open ayah 75:33ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡
أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰ
Open ayah 75:34የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡
ثُمَّ أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰٓ
Open ayah 75:35ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡
أَيَحۡسَبُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَن يُتۡرَكَ سُدًى
Open ayah 75:36ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን?
أَلَمۡ يَكُ نُطۡفَةٗ مِّن مَّنِيّٖ يُمۡنَىٰ
Open ayah 75:37የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?
ثُمَّ كَانَ عَلَقَةٗ فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ
Open ayah 75:38ከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡
فَجَعَلَ مِنۡهُ ٱلزَّوۡجَيۡنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰٓ
Open ayah 75:39ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡
أَلَيۡسَ ذَٰلِكَ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يُحۡـِۧيَ ٱلۡمَوۡتَىٰ
Open ayah 75:40ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?