المعارج
Al-Ma'aarij
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
سَأَلَ سَآئِلُۢ بِعَذَابٖ وَاقِعٖ
Open ayah 70:1ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡
لِّلۡكَٰفِرِينَ لَيۡسَ لَهُۥ دَافِعٞ
Open ayah 70:2በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡
مِّنَ ٱللَّهِ ذِي ٱلۡمَعَارِجِ
Open ayah 70:3የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡
تَعۡرُجُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَٱلرُّوحُ إِلَيۡهِ فِي يَوۡمٖ كَانَ مِقۡدَارُهُۥ خَمۡسِينَ أَلۡفَ سَنَةٖ
Open ayah 70:4መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡
فَٱصۡبِرۡ صَبۡرٗا جَمِيلًا
Open ayah 70:5መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡
إِنَّهُمۡ يَرَوۡنَهُۥ بَعِيدٗا
Open ayah 70:6እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡
وَنَرَىٰهُ قَرِيبٗا
Open ayah 70:7እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡
يَوۡمَ تَكُونُ ٱلسَّمَآءُ كَٱلۡمُهۡلِ
Open ayah 70:8ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡
وَتَكُونُ ٱلۡجِبَالُ كَٱلۡعِهۡنِ
Open ayah 70:9ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡
وَلَا يَسۡـَٔلُ حَمِيمٌ حَمِيمٗا
Open ayah 70:10ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡
يُبَصَّرُونَهُمۡۚ يَوَدُّ ٱلۡمُجۡرِمُ لَوۡ يَفۡتَدِي مِنۡ عَذَابِ يَوۡمِئِذِۭ بِبَنِيهِ
Open ayah 70:11(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡
وَصَٰحِبَتِهِۦ وَأَخِيهِ
Open ayah 70:12በሚስቱም በወንድሙም፡፡
وَفَصِيلَتِهِ ٱلَّتِي تُـٔۡوِيهِ
Open ayah 70:13በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡
وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا ثُمَّ يُنجِيهِ
Open ayah 70:14በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡
كَلَّآۖ إِنَّهَا لَظَىٰ
Open ayah 70:15ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡
نَزَّاعَةٗ لِّلشَّوَىٰ
Open ayah 70:16የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡
تَدۡعُواْ مَنۡ أَدۡبَرَ وَتَوَلَّىٰ
Open ayah 70:17(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡
وَجَمَعَ فَأَوۡعَىٰٓ
Open ayah 70:18ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡
۞إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ خُلِقَ هَلُوعًا
Open ayah 70:19ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡
إِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ جَزُوعٗا
Open ayah 70:20ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡
وَإِذَا مَسَّهُ ٱلۡخَيۡرُ مَنُوعًا
Open ayah 70:21መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡
إِلَّا ٱلۡمُصَلِّينَ
Open ayah 70:22ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡
ٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ دَآئِمُونَ
Open ayah 70:23እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡
وَٱلَّذِينَ فِيٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ حَقّٞ مَّعۡلُومٞ
Open ayah 70:24እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡
لِّلسَّآئِلِ وَٱلۡمَحۡرُومِ
Open ayah 70:25ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡
وَٱلَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ
Open ayah 70:26እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡
وَٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ
Open ayah 70:27እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡
إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمۡ غَيۡرُ مَأۡمُونٖ
Open ayah 70:28የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ
Open ayah 70:29እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡
إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ
Open ayah 70:30በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡
فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ
Open ayah 70:31ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ
Open ayah 70:32እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡
وَٱلَّذِينَ هُم بِشَهَٰدَٰتِهِمۡ قَآئِمُونَ
Open ayah 70:33እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡
وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ يُحَافِظُونَ
Open ayah 70:34እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡
أُوْلَٰٓئِكَ فِي جَنَّٰتٖ مُّكۡرَمُونَ
Open ayah 70:35እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡
فَمَالِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ قِبَلَكَ مُهۡطِعِينَ
Open ayah 70:36ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?
عَنِ ٱلۡيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ عِزِينَ
Open ayah 70:37ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡
أَيَطۡمَعُ كُلُّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ أَن يُدۡخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٖ
Open ayah 70:38ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?
كَلَّآۖ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّمَّا يَعۡلَمُونَ
Open ayah 70:39ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡
فَلَآ أُقۡسِمُ بِرَبِّ ٱلۡمَشَٰرِقِ وَٱلۡمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ
Open ayah 70:40በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡
عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ خَيۡرٗا مِّنۡهُمۡ وَمَا نَحۡنُ بِمَسۡبُوقِينَ
Open ayah 70:41ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡
فَذَرۡهُمۡ يَخُوضُواْ وَيَلۡعَبُواْ حَتَّىٰ يُلَٰقُواْ يَوۡمَهُمُ ٱلَّذِي يُوعَدُونَ
Open ayah 70:42ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡
يَوۡمَ يَخۡرُجُونَ مِنَ ٱلۡأَجۡدَاثِ سِرَاعٗا كَأَنَّهُمۡ إِلَىٰ نُصُبٖ يُوفِضُونَ
Open ayah 70:43ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡
خَٰشِعَةً أَبۡصَٰرُهُمۡ تَرۡهَقُهُمۡ ذِلَّةٞۚ ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلَّذِي كَانُواْ يُوعَدُونَ
Open ayah 70:44ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡