النبإ
An-Naba
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
عَمَّ يَتَسَآءَلُونَ
Open ayah 78:1ከምን ነገር ይጠያየቃሉ?
عَنِ ٱلنَّبَإِ ٱلۡعَظِيمِ
Open ayah 78:2ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡
ٱلَّذِي هُمۡ فِيهِ مُخۡتَلِفُونَ
Open ayah 78:3ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡
كَلَّا سَيَعۡلَمُونَ
Open ayah 78:4ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
ثُمَّ كَلَّا سَيَعۡلَمُونَ
Open ayah 78:5ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡
أَلَمۡ نَجۡعَلِ ٱلۡأَرۡضَ مِهَٰدٗا
Open ayah 78:6ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን?
وَٱلۡجِبَالَ أَوۡتَادٗا
Open ayah 78:7ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን?
وَخَلَقۡنَٰكُمۡ أَزۡوَٰجٗا
Open ayah 78:8ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡
وَجَعَلۡنَا نَوۡمَكُمۡ سُبَاتٗا
Open ayah 78:9እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡
وَجَعَلۡنَا ٱلَّيۡلَ لِبَاسٗا
Open ayah 78:10ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡
وَجَعَلۡنَا ٱلنَّهَارَ مَعَاشٗا
Open ayah 78:11ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡
وَبَنَيۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعٗا شِدَادٗا
Open ayah 78:12ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡
وَجَعَلۡنَا سِرَاجٗا وَهَّاجٗا
Open ayah 78:13አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡
وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلۡمُعۡصِرَٰتِ مَآءٗ ثَجَّاجٗا
Open ayah 78:14ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡
لِّنُخۡرِجَ بِهِۦ حَبّٗا وَنَبَاتٗا
Open ayah 78:15በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡
وَجَنَّٰتٍ أَلۡفَافًا
Open ayah 78:16የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡
إِنَّ يَوۡمَ ٱلۡفَصۡلِ كَانَ مِيقَٰتٗا
Open ayah 78:17የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡
يَوۡمَ يُنفَخُ فِي ٱلصُّورِ فَتَأۡتُونَ أَفۡوَاجٗا
Open ayah 78:18በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡
وَفُتِحَتِ ٱلسَّمَآءُ فَكَانَتۡ أَبۡوَٰبٗا
Open ayah 78:19ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡
وَسُيِّرَتِ ٱلۡجِبَالُ فَكَانَتۡ سَرَابًا
Open ayah 78:20ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡
إِنَّ جَهَنَّمَ كَانَتۡ مِرۡصَادٗا
Open ayah 78:21ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡
لِّلطَّٰغِينَ مَـَٔابٗا
Open ayah 78:22ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡
لَّٰبِثِينَ فِيهَآ أَحۡقَابٗا
Open ayah 78:23በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤
لَّا يَذُوقُونَ فِيهَا بَرۡدٗا وَلَا شَرَابًا
Open ayah 78:24በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡
إِلَّا حَمِيمٗا وَغَسَّاقٗا
Open ayah 78:25ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡
جَزَآءٗ وِفَاقًا
Open ayah 78:26ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡
إِنَّهُمۡ كَانُواْ لَا يَرۡجُونَ حِسَابٗا
Open ayah 78:27እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡
وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا كِذَّابٗا
Open ayah 78:28በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡
وَكُلَّ شَيۡءٍ أَحۡصَيۡنَٰهُ كِتَٰبٗا
Open ayah 78:29ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡
فَذُوقُواْ فَلَن نَّزِيدَكُمۡ إِلَّا عَذَابًا
Open ayah 78:30ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡
إِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ مَفَازًا
Open ayah 78:31ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡
حَدَآئِقَ وَأَعۡنَٰبٗا
Open ayah 78:32አትክልቶችና ወይኖችም፡፡
وَكَوَاعِبَ أَتۡرَابٗا
Open ayah 78:33እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡
وَكَأۡسٗا دِهَاقٗا
Open ayah 78:34የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡
لَّا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوٗا وَلَا كِذَّٰبٗا
Open ayah 78:35በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡
جَزَآءٗ مِّن رَّبِّكَ عَطَآءً حِسَابٗا
Open ayah 78:36ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡
رَّبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا ٱلرَّحۡمَٰنِۖ لَا يَمۡلِكُونَ مِنۡهُ خِطَابٗا
Open ayah 78:37የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡
يَوۡمَ يَقُومُ ٱلرُّوحُ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ صَفّٗاۖ لَّا يَتَكَلَّمُونَ إِلَّا مَنۡ أَذِنَ لَهُ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَقَالَ صَوَابٗا
Open ayah 78:38መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡
ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلۡحَقُّۖ فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ مَـَٔابًا
Open ayah 78:39ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡
إِنَّآ أَنذَرۡنَٰكُمۡ عَذَابٗا قَرِيبٗا يَوۡمَ يَنظُرُ ٱلۡمَرۡءُ مَا قَدَّمَتۡ يَدَاهُ وَيَقُولُ ٱلۡكَافِرُ يَٰلَيۡتَنِي كُنتُ تُرَٰبَۢا
Open ayah 78:40እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡