البلد
Al-Balad
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
لَآ أُقۡسِمُ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ
Open ayah 90:1በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡
وَأَنتَ حِلُّۢ بِهَٰذَا ٱلۡبَلَدِ
Open ayah 90:2አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡
وَوَالِدٖ وَمَا وَلَدَ
Open ayah 90:3በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡
لَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ فِي كَبَدٍ
Open ayah 90:4ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡
أَيَحۡسَبُ أَن لَّن يَقۡدِرَ عَلَيۡهِ أَحَدٞ
Open ayah 90:5በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን?
يَقُولُ أَهۡلَكۡتُ مَالٗا لُّبَدًا
Open ayah 90:6«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡
أَيَحۡسَبُ أَن لَّمۡ يَرَهُۥٓ أَحَدٌ
Open ayah 90:7አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን?
أَلَمۡ نَجۡعَل لَّهُۥ عَيۡنَيۡنِ
Open ayah 90:8ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን?
وَلِسَانٗا وَشَفَتَيۡنِ
Open ayah 90:9ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡
وَهَدَيۡنَٰهُ ٱلنَّجۡدَيۡنِ
Open ayah 90:10ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?
فَلَا ٱقۡتَحَمَ ٱلۡعَقَبَةَ
Open ayah 90:11ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡
وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا ٱلۡعَقَبَةُ
Open ayah 90:12ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
فَكُّ رَقَبَةٍ
Open ayah 90:13(እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡
أَوۡ إِطۡعَٰمٞ فِي يَوۡمٖ ذِي مَسۡغَبَةٖ
Open ayah 90:14ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡
يَتِيمٗا ذَا مَقۡرَبَةٍ
Open ayah 90:15የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤
أَوۡ مِسۡكِينٗا ذَا مَتۡرَبَةٖ
Open ayah 90:16ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡
ثُمَّ كَانَ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلصَّبۡرِ وَتَوَاصَوۡاْ بِٱلۡمَرۡحَمَةِ
Open ayah 90:17(ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡
أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَيۡمَنَةِ
Open ayah 90:18እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا هُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلۡمَشۡـَٔمَةِ
Open ayah 90:19እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
عَلَيۡهِمۡ نَارٞ مُّؤۡصَدَةُۢ
Open ayah 90:20በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡