العاديات
Al-Aadiyaat
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
وَٱلۡعَٰدِيَٰتِ ضَبۡحٗا
Open ayah 100:1እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡
فَٱلۡمُورِيَٰتِ قَدۡحٗا
Open ayah 100:2(በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤
فَٱلۡمُغِيرَٰتِ صُبۡحٗا
Open ayah 100:3በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤
فَأَثَرۡنَ بِهِۦ نَقۡعٗا
Open ayah 100:4በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤
فَوَسَطۡنَ بِهِۦ جَمۡعًا
Open ayah 100:5በ(ጠላት) ክቢ መካከል በእርሱ (በጧት) በተጋፈጡትም እምላለሁ፡፡
إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لِرَبِّهِۦ لَكَنُودٞ
Open ayah 100:6ሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡
وَإِنَّهُۥ عَلَىٰ ذَٰلِكَ لَشَهِيدٞ
Open ayah 100:7እርሱም በዚህ ላይ መስካሪ ነው፡፡
وَإِنَّهُۥ لِحُبِّ ٱلۡخَيۡرِ لَشَدِيدٌ
Open ayah 100:8እርሱም ገንዘብን ለመውደድ በጣም ብርቱ ነው፡፡
۞أَفَلَا يَعۡلَمُ إِذَا بُعۡثِرَ مَا فِي ٱلۡقُبُورِ
Open ayah 100:9(ሰው) አያውቅምን? በመቃብሮች ያሉት (ሙታን) በተቀሰቀሱ ጊዜ፤
وَحُصِّلَ مَا فِي ٱلصُّدُورِ
Open ayah 100:10በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ (እንዴት እንደሚኾን)፡፡
إِنَّ رَبَّهُم بِهِمۡ يَوۡمَئِذٖ لَّخَبِيرُۢ
Open ayah 100:11ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡