العلق
Al-Alaq
Translation: Amharic - Sadiq/Sani Habib · Open the surah
بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
ٱقۡرَأۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلَّذِي خَلَقَ
Open ayah 96:1አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡
خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِنۡ عَلَقٍ
Open ayah 96:2ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡
ٱقۡرَأۡ وَرَبُّكَ ٱلۡأَكۡرَمُ
Open ayah 96:3አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤
ٱلَّذِي عَلَّمَ بِٱلۡقَلَمِ
Open ayah 96:4ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡
عَلَّمَ ٱلۡإِنسَٰنَ مَا لَمۡ يَعۡلَمۡ
Open ayah 96:5ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡
كَلَّآ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَيَطۡغَىٰٓ
Open ayah 96:6በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡
أَن رَّءَاهُ ٱسۡتَغۡنَىٰٓ
Open ayah 96:7ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡
إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلرُّجۡعَىٰٓ
Open ayah 96:8መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
أَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي يَنۡهَىٰ
Open ayah 96:9አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡
عَبۡدًا إِذَا صَلَّىٰٓ
Open ayah 96:10ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤
أَرَءَيۡتَ إِن كَانَ عَلَى ٱلۡهُدَىٰٓ
Open ayah 96:11አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤
أَوۡ أَمَرَ بِٱلتَّقۡوَىٰٓ
Open ayah 96:12ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤
أَرَءَيۡتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰٓ
Open ayah 96:13አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤
أَلَمۡ يَعۡلَم بِأَنَّ ٱللَّهَ يَرَىٰ
Open ayah 96:14አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?
كَلَّا لَئِن لَّمۡ يَنتَهِ لَنَسۡفَعَۢا بِٱلنَّاصِيَةِ
Open ayah 96:15ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡
نَاصِيَةٖ كَٰذِبَةٍ خَاطِئَةٖ
Open ayah 96:16ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡
فَلۡيَدۡعُ نَادِيَهُۥ
Open ayah 96:17ሸንጎውንም ይጥራ፡፡
سَنَدۡعُ ٱلزَّبَانِيَةَ
Open ayah 96:18(እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡
كَلَّا لَا تُطِعۡهُ وَٱسۡجُدۡۤ وَٱقۡتَرِب۩
Open ayah 96:19ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡